ዘዳግም 11:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህች የምትወርሳት ምድር ከዚህ በፊት እንደ ነበርክባት እንደ ግብጽ ምድር አይደለችም። በግብጽ ምድር እህል ከዘራህ በኋላ እንደ ጓሮ አትክልት ማሳውን ውሃ ለማጠጣት ቦዩን በእግርህ አማካይነት ትቈጣጠረው ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የምትገባባት ምድር እንደ ወጣህባትና ዘርህን ዘርተህባት በእግርህ ውሃ እንዳጠጣሃት የአትክልት ቦታ እንደ ግብጽ ምድር አይደለችም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የምትገባባት ምድር እንደ ወጣህባትና ዘርህን ዘርተህባት በእግርህ ውሃ እንዳጠጣሃት የአትክልት ቦታ እንደ ግብጽ ምድር አይደለችም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ትወርሳት ዘንድ የምትገባባት ምድር፥ በአትክልት ስፍራ እንደሚዘሩ ዘርህን እንደ ዘራህባት፥ በእግርህም እንዳጠጣሃት፥ እንደ ወጣህባት እንደ ግብፅ ምድር አይደለችም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ትወርሳት ዘንድ የምትገባባት ምድር፥ በአትክልት ስፍራ እንደሚዘሩ ዘርህን እንደዘራህባት፥ በእግርህም እንዳጠጣሃት፥ እንደ ወጣህባት እንደ ግብፅ ምድር አይደለችም። |
የምታስገኘውን ሰብልና ሌሎችን መልካም ነገሮች ሁሉ አግኝተው እንዲደሰቱ ለም ወደ ሆነች ምድር አገባኋቸው፤ እነርሱ ግን ምድሬን አበላሹ፤ የሰጠኋቸውን አገር አረከሱ።
ግብጻውያንም በዓሉን ለማክበር ወደ ኢየሩሳሌም ወጥተው በእግዚአብሔር ፊት መቅረብ ባይፈልጉ፥ “ወደ ኢየሩሳሌም ወጥተን የዳስ በዓል አናከብርም” በሚሉ መንግሥታት ላይ የሚደርሰው ቀሣፊ በሽታ ይመጣባቸዋል።
ትእዛዞቹንም ብትጠብቁ እግዚአብሔር ለቀድሞ አባቶቻችሁና ለዘሮቻቸው ሊሰጣቸው ቃል በገባላቸው በማርና በወተት በበለጸገችው፥ በዚያች ለምለም ምድር ለረጅም ዘመን ትኖራላችሁ።
እነሆ፥ አምላክህ እግዚአብሔር ወደ መልካሚቱ ለምለም ምድር ሊያስገባህ አምጥቶሃል፤ ያቺም ምድር ከሸለቆዎችና ከኮረብቶች የሚመነጩ ወንዞችና ጅረቶች፥ ፈሳሾች ምንጮችም ይገኙበታል፤