ኪራም የሰሎሞን መልእክት ሲደርሰው እጅግ ስለ ተደሰተ፥ “በእርሱ እግር ተተክቶ በዚህ በታላቅ ሕዝብ ላይ እንዲነግሥ ይህን የመሰለ ጥበበኛ ልጅ ለዳዊት የሰጠ እግዚአብሔር ይመስገን!” አለ፤
ዳንኤል 6:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሡም እጅግ ደስ አለው፤ ዳንኤልንም ከጒድጓዱ ውስጥ እንዲያወጡት ትእዛዝ ሰጠ፤ ባወጡትም ጊዜ በእግዚአብሔር በመታመኑ በሰውነቱ ላይ ምንም ጒዳት እንዳልደረሰበት ታወቀ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሡ እጅግ ተደስቶ፤ ዳንኤልን ከጕድጓዱ እንዲያወጡት አዘዘ። ዳንኤል በአምላኩ ታምኖ ነበርና ከጕድጓድ በወጣ ጊዜ፣ አንዳች ጕዳት አልተገኘበትም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዚያን ጊዜም ንጉሡ እጅግ ደስ አለው፥ ዳንኤልንም ከጕድጓዱ ያወጡት ዘንድ አዘዘ፥ ዳንኤልም ከጕድጓድ ወጣ፥ በአምላኩም ታምኖ ነበርና አንዳች ጉዳት አልተገኘበትም። |
ኪራም የሰሎሞን መልእክት ሲደርሰው እጅግ ስለ ተደሰተ፥ “በእርሱ እግር ተተክቶ በዚህ በታላቅ ሕዝብ ላይ እንዲነግሥ ይህን የመሰለ ጥበበኛ ልጅ ለዳዊት የሰጠ እግዚአብሔር ይመስገን!” አለ፤
እምነታቸውንም በእግዚአብሔር አድርገው እርሱ እንዲረዳቸው ተማጠኑት፤ እግዚአብሔርም ጸሎታቸውን ሰምቶ፥ በሀጋራውያንና በእነርሱም የጦር ጓደኞች ላይ ድልን አጐናጸፋቸው፤
ሰዎቹ በማግስቱ ጠዋት በማለዳ ተነሥተው ተቆዓ ተብሎ ከሚጠራ ስፍራ አጠገብ ወደሚገኘው በረሓማ አገር ሄዱ፤ ወደዚያ ለመሄድ ጒዞ በመጀመር ላይ ሳሉም ኢዮሣፍጥ እነርሱን “የይሁዳና የኢየሩሳሌም ሰዎች ሆይ! በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ተማመኑ፤ እርሱም ብርታትን ይሰጣችኋል፤ የእግዚአብሔር ነቢያት የሚነግሩአችሁንም እመኑ፤ ይሳካላችኋልም” አላቸው።
ንጉሡም “እነሆ፥ እኔ እሳቱ ምንም ሳይጐዳቸው ከእስራት ተፈተው በነበልባሉ ውስጥ የሚመላለሱ አራት ሰዎች አያለሁ፤ አራተኛውም የአማልክትን ልጅ ይመስላል” አለ።
ንጉሡም ይህን በሰማ ጊዜ እጅግ አዘነ፤ ዳንኤልንም ለማዳን ወሰነ፤ ፀሐይም እስክትጠልቅ ድረስ እርሱን ለማዳን የሚችልበትን ዘዴ ሁሉ ለማግኘት ሞከረ።