ዳንኤል 3:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያን በኋላ ንጉሡ ናቡከደነፆር በመደነቅ ፈጥኖ ተነሣና “አስረን በሚነደው የእሳት ነበልባል ውስጥ የጣልናቸው ሰዎች ሦስት ብቻ አልነበሩምን?” ሲል አማካሪዎቹን ጠየቀ። እነርሱም “አዎ፥ ንጉሥ ሆይ!” አሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ በኋላ ንጉሥ ናቡከደነፆር በአድናቆት ከተቀመጠበት ዘልሎ በመነሣት አማካሪዎቹን “አስረን በእሳት ውስጥ የጣልናቸው ሰዎች ሦስት አልነበሩምን?” ሲል ጠየቀ። እነርሱም፣ “ንጉሥ ሆይ፤ እውነት ነው” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዚያን ጊዜም ንጉሡ ናቡከደነፆር ተደነቀ ፈጥኖም ተነሣ፥ አማካሪዎቹንም፦ ሦስት ሰዎች አስረን በእሳት ውስጥ ጥለን አልነበረምን? ብሎ ተናገራቸው። እነርሱም፦ ንጉሥ ሆይ፥ እውነት ነው ብለው ለንጉሡ መለሱለት። |
ንጉሡም “እነሆ፥ እኔ እሳቱ ምንም ሳይጐዳቸው ከእስራት ተፈተው በነበልባሉ ውስጥ የሚመላለሱ አራት ሰዎች አያለሁ፤ አራተኛውም የአማልክትን ልጅ ይመስላል” አለ።
“ንጉሥ ሆይ! ረጅምና ብርቱ የሆነው ያ ዛፍ አንተ ነህ፤ ታላቅነትህ እስከ ሰማይ ከፍ ከፍ ብሎአል፤ ሥልጣንህም በዓለም ሁሉ ላይ ተንሰራፍቶአል።
ስለዚህ ንጉሥ ሆይ! በበኩሌ የምመክርህን ስማ፤ ኃጢአት መሥራትን ትተህ መልካም ሥራ መሥራትን አዘወትር፤ ክፋትን ትተህ ለተጨቈኑ ሰዎች ራራላቸው፤ ይህን ብታደርግ በሰላም የመኖር ዕድሜህ ይረዝምልህ ይሆናል።”
አንበሶቹ እንዳይጐዱኝ እግዚአብሔር መልአኩን ልኮ አፋቸውን ዘጋ፤ ይህንንም ያደረገው እኔ በእርሱ ዘንድ ንጹሕ መሆኔንና አንተንም አለመበደሌን ስላወቀ ነው።”
እኛ በመንግሥትህ አስተዳደር ሥራ ላይ የተመደብን የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣኖች፥ ዐቃብያነ ሕግ፥ እንደራሴዎች፥ አማካሪዎችና አገረ ገዢዎች የተስማማንበት አንድ ነገር አለ፤ ይኸውም ከአሁን ጀምሮ እስከ ሠላሳ ቀን ድረስ ወደ አንተ ካልሆነ በቀር ወደማንኛውም አምላክ ወይም ሰው ጸሎት እንዳይደረግ ዐዋጅ እንድታስነግር ነው፤ ይህንንም ዐዋጅ የሚተላለፍ ቢኖር በአንበሶች ጒድጓድ እንዲጣል እዘዝ።
ንጉሥ ሆይ! በመንገድ ሳለሁ ልክ እኩለ ቀን ሲሆን ከፀሐይ ብርሃን የሚበልጥ ብርሃን አየሁ፤ ይህም ብርሃን በእኔና ከእኔ ጋር በሚጓዙት ሰዎች ዙሪያ ከሰማይ አበራ።
ዳዊት ጎልያድን ለመውጋት በሚሄድበት ጊዜ ሳኦል ተመልክቶ የጦሩን አዛዥ አበኔርን “ይህ የማን ልጅ ነው?” ሲል ጠየቀው። አበኔርም “ንጉሥ ሆይ! በሕይወትህ እምላለሁ፤ የማን ልጅ እንደ ሆነ ገና አላወቅሁም” አለው።