ዳንኤል 2:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ዳንኤል ወደ ቤቱ ሄደና የሆነውን ነገር ለጓደኞቹ ለሐናንያ፥ ለሚሳኤልና ለዐዛርያ ነገራቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ በኋላ ዳንኤል ወደ ቤቱ ተመልሶ ለጓደኞቹ ለአናንያ፣ ለሚሳኤልና ለአዛርያ ነገሩን ገለጠላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዚያን ጊዜም ዳንኤል ወደ ቤቱ ሄደ። ዳንኤልም ባልንጀሮቹም ከቀሩት ከባቢሎን ጠቢባን ጋር እንዳይሞቱ ስለዚህ ምሥጢር ምሕረትን ከሰማይ አምላክ ይለምኑ ዘንድ ነገሩን ለባልንጀሮቹ ለአናንያና ለሚሳኤል ለአዛርያ አስታወቃቸው። |
እነሆ፥ በባቢሎን አውራጃዎች ላይ ገዢዎች አድርገህ የሾምካቸው ሲድራቅ፥ ሚሳቅና አብደናጎ የተባሉ የአይሁድ ወገኖች የአንተን ትእዛዝ አይፈጽሙም፤ አማልክትህን አያመልኩም፤ ላቆምከውም ምስል አይሰግዱም።”
“እንደዚህ የሚታደግ ሌላ አምላክ የለም፤ ስለዚህ በአገሮች ሁሉ በሚኖሩና ልዩ ልዩ ቋንቋዎችን በሚናገሩ ሕዝቦች ሁሉ መካከል በሲድራቅ፥ በሚሳቅና በአብደናጎ አምላክ ላይ የስድብ ቃል የሚናገር ቢኖር ሰውነቱ ተቈራርጦ እንዲጣልና ቤቱም የፍርስራሽ ክምር እንዲሆን ዐውጃለሁ።”