ዳንኤልም ወዲያውኑ ገብቶ ሕልሙን ለመተርጐም ጥቂት ጊዜ እንዲሰጠው ንጉሡን ለመነ።
በዚህ ጊዜ፣ ዳንኤልም ገብቶ ሕልሙን ይተረጕምለት ዘንድ ጊዜ እንዲሰጠው ንጉሡን ጠየቀው።
ዳንኤልም ገብቶ ፍቺውን ለንጉሡ የሚያስታውቅበት ጊዜ ይሰጠው ዘንድ ንጉሡን ለመነ።
የንጉሥ ቊጣ የሞት መልእክተኛ ነው። ብልኅ ሰው ግን ቊጣውን ያበርዳል።
“ንጉሡ ይህን ከባድ ውሳኔ ያስተላለፈው እንዴት ነው?” ብሎ ጠየቀው፤ አርዮክም ጉዳዩን ለዳንኤል ገልጦ አስረዳው።
ከዚህ በኋላ ዳንኤል ወደ ቤቱ ሄደና የሆነውን ነገር ለጓደኞቹ ለሐናንያ፥ ለሚሳኤልና ለዐዛርያ ነገራቸው።