ቈላስይስ 4:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእርሱም ጋር የእናንተ ወገን የሆነው የታመነውና የተወደደው ወንድም ኦኔሲሞስ ወደ እናንተ ይመጣል፤ እነርሱ በዚህ ስፍራ ስላለው ነገር ሁሉ ያስታውቋችኋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም ከእናንተ ወገን ከሆነው ከታማኙና ከተወዳጁ ወንድማችን ከአናሲሞስ ጋራ ወደ እናንተ ይመጣል፤ እነርሱም እዚህ ስላለው ሁኔታ ሁሉ ይነግሯችኋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቲቂቆስም ከእናንተ ወገን ከሆነውና ከታመነው ከተወደደውም ወንድም ከኦኔሲሞስ ጋር አብሮ ይመጣል። በእዚህም ሥፍራ ስላለው ሁኔታ ሁሉ ያስታውቋችኋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወገናችሁ ከሆነው ከምንወደውና ከታመነው ወንድማችን ከአናሲሞስ ጋር፥ እነርሱ ሥራችንንና ያለንበትን ያስረዱአችኋል። |
የእናንተ ወገን የሆነው የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ኤጳፍራም ሰላምታ ያቀርብላችኋል፤ በመንፈሳዊ ሕይወት በማደግ ጸንታችሁ እንድትቆሙና የእግዚአብሔርንም ፈቃድ በሙሉ እንድትፈጽሙ እርሱ ስለ እናንተ በጸሎቱ ዘወትር ይጸልያል።