በአንድ ከተማ መከራ ሲያበዙባችሁ፥ ወደ ሌላው ሽሹ፤ በእውነት እላችኋለሁ የሰው ልጅ ተመልሶ እስኪመጣ ድረስ የእስራኤልን ከተሞች ሁሉ አታዳርሱም።
ሐዋርያት ሥራ 8:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የተበተኑትም አማኞች በሄዱበት ስፍራ ሁሉ የእግዚአብሔርን ቃል ያስተምሩ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የተበተኑትም በሄዱበት ሁሉ ቃሉን ሰበኩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የተበተኑትም ቃሉን እየሰበኩ ዞሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የተበተኑት ግን እየተዘዋወሩ የእግዚአብሔርን ቃል ሰበኩ፥ አስተማሩም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የተበተኑትም ቃሉን እየሰበኩ ዞሩ። |
በአንድ ከተማ መከራ ሲያበዙባችሁ፥ ወደ ሌላው ሽሹ፤ በእውነት እላችኋለሁ የሰው ልጅ ተመልሶ እስኪመጣ ድረስ የእስራኤልን ከተሞች ሁሉ አታዳርሱም።
እስጢፋኖስ ተወግሮ በሞተ ጊዜ በተነሣው ስደት ምክንያት የተበተኑት አማኞች እስከ ፊንቄና እስከ ቆጵሮስ እስከ አንጾኪያም ሄዱ፤ ቃሉንም ለአይሁድ ብቻ እንጂ ለሌሎች አይናገሩም ነበር።
ሳውልም በእስጢፋኖስ መገደል ተስማምቶ ነበር፤ እስጢፋኖስ በሞተበት ቀን በኢየሩሳሌም በምትገኘው ቤተ ክርስቲያን ላይ ታላቅ ስደት ተነሣ፤ ከሐዋርያት በቀር አማኞች ሁሉ ወደ ይሁዳና ወደ ሰማርያ ምድር ተበተኑ።
ነገር ግን ፊልጶስ ስለ እግዚአብሔር መንግሥትና ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም የተናገረውን መልካም ዜና በሰሙ ጊዜ ወንዶችም ሴቶችም አምነው ተጠመቁ።
እናንተ እንደምታውቁት ከዚህ ቀደም በፊልጵስዩስ በነበርንበት ጊዜ መከራና ስድብ ደርሶብናል፤ ነገር ግን ታላቅ ተቃውሞ ቢደርስብንም እንኳ ወንጌሉን ለእናንተ እንድናስተምር አምላካችን ድፍረትን ሰጥቶናል።