“እኔ በኪልቅያ በምትገኘው በጠርሴስ ከተማ የተወለድኩ አይሁዳዊ ነኝ፤ ያደግኹት ግን በዚህች በኢየሩሳሌም ከተማ ነው። አስተማሪዬም ገማልያል ነበር፤ የአባቶችን ሕግ ጠንቅቄ የተማርኩና ልክ ዛሬ እናንተ እንደምታደርጉት እግዚአብሔርን በመንፈሳዊ ቅናት የማገለግል ነበርኩ።
ሐዋርያት ሥራ 26:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ከልጅነቴ ጀምሮ እንዴት እንደ ኖርኩ አይሁድ ያውቃሉ፤ ከመጀመሪያ አንሥቶ በሕዝቤ መካከልና በኢየሩሳሌም የኖርኩትን ሕይወቴን ያውቁታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ገና ከልጅነቴ ጀምሮ፣ በአገሬም ሆነ በኢየሩሳሌም እንዴት እንደ ኖርሁ አይሁድ ሁሉ ያውቃሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ከመጀመሪያ አንሥቶ በሕዝቤ መካከል በኢየሩሳሌም የሆነውን፥ ከታናሽነቴ ጀምሬ የኖርሁትን ኑሮዬን አይሁድ ሁሉ ያውቃሉ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ከልጅነቴ ጀምሮ በወገኖች መካከል በኢየሩሳሌም የኖርሁትን ኑሮ አይሁድ ሁሉ ያውቃሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከመጀመሪያ አንሥቶ በሕዝቤ መካከል በኢየሩሳሌም የሆነውን፥ ከታናሽነቴ ጀምሬ የኖርሁትን ኑሮዬን አይሁድ ሁሉ ያውቃሉ፤ |
“እኔ በኪልቅያ በምትገኘው በጠርሴስ ከተማ የተወለድኩ አይሁዳዊ ነኝ፤ ያደግኹት ግን በዚህች በኢየሩሳሌም ከተማ ነው። አስተማሪዬም ገማልያል ነበር፤ የአባቶችን ሕግ ጠንቅቄ የተማርኩና ልክ ዛሬ እናንተ እንደምታደርጉት እግዚአብሔርን በመንፈሳዊ ቅናት የማገለግል ነበርኩ።
ነገር ግን ይህን ልገልጥልህ እወዳለሁ፤ እነርሱ አዲስ መንገድ በሚሉት የሃይማኖት ክፍል እምነት የአባቶቻችንን አምላክ አመልካለሁ፤ በሕግና በነቢያት መጻሕፍት የተጻፈውንም ሁሉ አምናለሁ።
ቀድሞ የአይሁድ እምነት ተከታይ በነበርኩበት ጊዜ እንዴት እንደ ኖርኩ ሰምታችኋል፤ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ከመጠን በላይ እያሳደድኩ ለማጥፋት እጥር ነበር።
እኔ በተወለድኩ በስምንተኛው ቀን ተገርዤአለሁ፤ በትውልዴም ከብንያም ነገድ የሆንኩ እስራኤላዊ ነኝ፤ ከዚህም የተነሣ ጥርት ያልኩ ዕብራዊ ነኝ። የአይሁድን ሕግ ስለ መጠበቅም ቢሆን ፈሪሳዊ ነበር።