ሐዋርያት ሥራ 26:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አግሪጳ ጳውሎስን “ስለ ራስህ እንድትናገር ተፈቅዶልሃል” አለው፤ ጳውሎስም እጁን ዘረጋና እንዲህ ሲል የመከላከያ መልሱን ሰጠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አግሪጳም ጳውሎስን፣ “ስለ ራስህ እንድትናገር ተፈቅዶልሃል” አለው። በዚህ ጊዜ ጳውሎስ እጁን ዘርግቶ እንዲህ ሲል መከላከያውን አቀረበ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አግሪጳም ጳውሎስን “ስለ ራስህ ትናገር ዘንድ ተፈቅዶልሃል፤” አለው። በዚያን ጊዜ ጳውሎስ እጁን ዘርግቶ እንዲህ ሲል መለሰ፦ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አግሪጳም ጳውሎስን፥ “ስለ ራስህ ትናገር ዘንድ ፈቅደንልሃል” አለው፤ ከዚህም በኋላ ጳውሎስ እጁን አነሣና ይነግራቸው ጀመር፤ እንዲህም አለ፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አግሪጳም ጳውሎስን፦ “ስለ ራስህ ትናገር ዘንድ ተፈቅዶልሃል” አለው። በዚያን ጊዜ ጳውሎስ እጁን ዘርግቶ መለሰ እንዲህ ሲል፦ |
“አሁን ግን አንቺን ለመቅጣትና ድርሻሽ የሆነውንም በረከት ከአንቺ ለመቀነስ እጄን ዘርግቼአለሁ፤ እነርሱ የፈለጉትን እንዲያደርጉ አንቺን ለጠላቶችሽ፥ ብልግናሽ ለሚያስደነግጣቸው ለፍልስጥኤማውያን አሳልፌ ሰጥቼሻለሁ።
እኔ ግን ‘ተከሳሽ ከከሳሾች ፊት ቆሞ ለተከሰሰበት ነገር የመከላከያ መልስ ሳይሰጥ ተከሳሹን አሳልፎ መስጠት የሮማውያን ሥርዓት አይደለም’ ብዬ መለስኩላቸው።
ጌታም ሐናንያን እንዲህ አለው፦ “እርሱ ስሜን ለአረማውያን፥ ለነገሥታትና ለእስራኤል ሰዎች የሚያሳውቅ፥ የእኔ ምርጥ መሣሪያ ስለ ሆነ ወደ እርሱ ሂድ፤