ሐዋርያት ሥራ 20:34 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በገዛ እጆቼ እየሠራሁ ራሴንም ሆነ ጓደኞቼን እረዳ እንደ ነበር እናንተ ራሳችሁ ታውቃላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነዚህ እጆቼ ለእኔና ከእኔ ጋራ ላሉት በሚያስፈልገን ነገር እንዳገለገሉን እናንተ ራሳችሁ ታውቃላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነዚህ እጆቼ በሚያስፈልገኝ ነገር ለእኔና ከእኔ ጋር ላሉት እንዳገለገሉ እናንተ ታውቃላችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነዚህም እጆች ለምሻው ነገርና ከእኔም ጋር ላሉት እንዳገለገሉ እናንተ ታውቃላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነዚህ እጆቼ በሚያስፈልገኝ ነገር ለእኔና ከእኔ ጋር ላሉት እንዳገለገሉ እናንተ ታውቃላችሁ። |
ከተማዋም በሙሉ ተሸበረች፤ ሕዝቡም የመቄዶንያ ተወላጆች የሆኑትን ሁለቱን የጳውሎስን የጒዞ ጓደኞች፥ ጋይዮስንና አርስጥሮኮስን ይዘው እየጐተቱ ወደ ሕዝብ መሰብሰቢያ ቦታ ሮጡ።
‘ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ የተባረከ ነው’ የሚለውን የጌታ ኢየሱስን ቃል በማስታወስ፥ በእጃችን እየሠራን ደካሞችን መርዳት እንደሚገባን በብዙ መንገድ አሳይቻችኋለሁ።”
ወንድሞች ሆይ! እንዴት እንደ ሠራንና እንደ ደከምን ታውቃላችሁ፤ የእግዚአብሔርን ወንጌል ለእናንተ በምናበሥርበት ጊዜ በአንዳችሁም ላይ ሸክም እንዳንሆን ሌሊትና ቀን በመሥራት እንደክም ነበር።
ከእኔ ጋር ያሉት ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡልሃል፤ በእምነት ከእኛ ጋር ተካፋይ ለሆኑ ወዳጆቻችን ሁሉ ሰላምታ አቅርብልን። የእግዚአብሔር ጸጋ ከሁላችሁም ጋር ይሁን።