ሐዋርያት ሥራ 2:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንዳንዶቹ ግን “አዲስ የወይን ጠጅ ጠጥተው ሰክረዋል!” እያሉ አፌዙባቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንዳንዶቹ ደግሞ “ያልፈላ ብዙ የወይን ጠጅ ጠጥተዋል” በማለት አፌዙባቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሌሎች ግን እያፌዙባቸው “ጉሽ የወይን ጠጅ ጠግበዋል፤” አሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኩሌቶቹ ግን “እነዚህስ ጉሽ ጠጅ ጠግበው ሰክረዋል” ብለው ሳቁባቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሌሎች ግን እያፌዙባቸው፦ “ጉሽ የወይን ጠጅ ጠግበዋል” አሉ። |
የአፍሽም መዓዛ እንደ መልካም ወይን ጠጅ ነው። እንግዲያውስ መልካሙ የወይን ጠጅ በውዴ ከንፈሮችና ጥርሶች መካከል እየተንቆረቆረ በዝግታ ይውረድ።
የሠራዊት አምላክ በዚህች በጽዮን ተራራ ለዓለም ሕዝቦች ሁሉ ታላቅ ግብዣ ያዘጋጃል፤ በግብዣውም ላይ ምርጥ የወይን ጠጅና፥ የተሟላ ምግብ ይዘጋጃል።
የእስራኤል ሕዝብ እንደ ብርቱ ጦረኞች ይሆናሉ፤ የወይን ጠጅ እንደ ጠጣ ሰውም ደስተኞች ይሆናሉ፤ ልጆቻቸውም ይህን ድል በማስታወስ ደስ ይላቸዋል፤ በእግዚአብሔርም ሐሤት ያደርጋሉ።
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ይከላከልላቸዋል፤ እነርሱም ጠላቶቻቸውን ይደመስሳሉ፤ የጠላትንም የወንጭፍ ድንጋይ ይረጋግጣሉ፤ የወይን ጠጅ ጠጥቶ እንደ ሰከረ ሰው ይጮኻሉ፤ የጠላቶቻቸውም ደም የመሥዋዕት ደም በሳሕን ሞልቶ በመሠዊያ ላይ እንደሚፈስስ ይፈስሳል።
ክርስቲያኖች በሚሰበሰቡበት ጊዜ እያንዳንዱ ክርስቲያን በተለያዩ ቋንቋዎች ቢናገርና የማያውቁ ወይም የማያምኑ ሰዎች ቢመጡ ተናጋሪዎችን “እነዚህ ሰዎች አብደዋል” አይሉምን?