ሐዋርያት ሥራ 18:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ረዘም ላለ ጊዜ ከእነርሱ ጋር እንዲቈይ ቢለምኑትም እሺ አላላቸውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእነርሱ ጋራ እንዲሰነብት በጠየቁትም ጊዜ ፈቃደኛ አልሆነም፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም ብዙ ጊዜ እንዲቀመጥላቸው ሲለምኑት እሺ አላለም፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም ብዙ ጊዜ እንዲሰነብት ማለዱት፤ ነገር ግን አልወደደም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም ብዙ ጊዜ እንዲቀመጥላቸው ሲለምኑት እሺ አላለም፤ |
ጳውሎስ በእስያ ጊዜ እንዳያባክን ብሎ ኤፌሶንን አልፎ ለመሄድ ፈለገ፤ ይህንንም ያደረገው ለጰንጠቆስጤ በዓል በኢየሩሳሌም ለመገኘት አስቦ ስለ ነበር ነው።
ወንድማችን አጵሎስ ከሌሎች ወንድሞች ጋር እናንተን እንዲጐበኛችሁ በጥብቅ ለምኜው ነበር፤ ነገር ግን እርሱ አሁን ወደ እናንተ ለመምጣት አልፈቀደም፤ ሲመቸው ግን ይመጣል።