ሐዋርያት ሥራ 10:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደግሞም “እግዚአብሔር ንጹሕ ያደረገውን አንተ ርኩስ ነው ማለት አይገባህም” የሚል ድምፅ እንደገና ሰማ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያም ድምፅ እንደ ገና ለሁለተኛ ጊዜ ወደ እርሱ መጥቶ፣ “እግዚአብሔር ንጹሕ ያደረገውን አንተ እንደ ርኩስ አትቍጠረው” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደግሞም ሁለተኛ “እግዚአብሔር ያነጻውን አንተ አታርክሰው፤” የሚል ድምፅ ወደ እርሱ መጣ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳግመኛም፥ “እግዚአብሔር ንጹሕ ያደረገውን አንተ አታርክስ” የሚል ቃል ወደ እርሱ መጣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞም ሁለተኛ፦ “እግዚአብሔር ያነጻውን አንተ አታርክሰው” የሚል ድምፅ ወደ እርሱ መጣ። |
እንዲህም አላቸው፦ “አይሁዳዊ ለሆነ ሰው ከሌላ ሕዝብ ጋር ለመተባበርና ወደ ቤቱም ለመግባት በሃይማኖታችን ሕግ እንደማይፈቀድ እናንተ ራሳችሁ ታውቃላችሁ፤ ነገር ግን ማንንም ንጹሕ ያልሆነ ወይም ርኩስ እንዳልል እግዚአብሔር ገልጦልኛል።
ይልቅስ ‘ለጣዖት በመሠዋቱ ምክንያት የረከሰ ምግብን አትብሉ፤ ከዝሙት ራቁ፤ ሳይታረድና ደሙም ሳይፈስ ታንቆ የሞተ እንስሳ ሥጋን አትብሉ፤ ደምንም አትብሉ’ ብለን እንጻፍላቸው።
ለጣዖት በመሠዋቱ ምክንያት የረከሰ ምግብ አትብሉ፤ ታንቆ የሞተ እንስሳ ሥጋን አትብሉ፤ ደምም አትብሉ፤ ከዝሙት ራቁ፤ ከእነዚህ ነገሮች ሁሉ ብትጠበቁ መልካም ታደርጋላችሁ፤ ደኅና ሁኑ።”
አንድን ነገር ርኩስ ነው ብሎ ለሚያስብ ሰው ያ ነገር ለእርሱ ርኩስ ይሆንበታል እንጂ ማንኛውም ነገር በራሱ ርኩስ እንዳልሆነ እኔ በጌታ ኢየሱስ ዐውቄ አረጋግጣለሁ።
በምግብም ምክንያት የእግዚአብሔርን ሥራ አናፍርስ። ምግብ ሁሉ ንጹሕ ነው፤ ነገር ግን ሌላውን ሰው የሚያሰናክል ምግብ መብላት ስሕተት ነው።
ለንጹሖች፥ ሁሉ ነገር ንጹሕ ነው፤ ለርኩሶችና ለማያምኑ ሰዎች ግን ንጹሕ የሆነ ምንም ነገር የለም፤ እንዲያውም አእምሮአቸውም ሆነ ኅሊናቸው የረከሰ ነው።
ከከተማው ውጪ ባለው በወይን መጭመቂያም ተጨመቀ፤ ከመጭመቂያውም እስከ ፈረስ ልጓም ወደ ላይ ከፍ ያለና ሦስት መቶ ኪሎ ሜትር ርቀት የሚደርስ ደም ወጥቶ ፈሰሰ።