La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ሳሙኤል 6:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ናኮን ተብሎ ወደሚጠራውም አውድማ በደረሱ ጊዜ ሠረገላውን የሚስቡት በሬዎች ስለ ነቀነቁት ዑዛ እጁን ዘርግቶ የቃል ኪዳኑ ታቦት እንዳይወድቅ ደገፈ፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ወደ ናኮን ዐውድማ ሲደርሱም በሬዎቹ ስለ ተደናቀፉ፣ ዖዛ እጁን ዘርግቶ የእግዚአብሔርን ታቦት ያዘ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ወደ ናኮን አውድማ ሲደርሱም በሬዎቹ ስለተደናቀፉ፥ ዖዛ እጁን ዘርግቶ የእግዚአብሔርን ታቦት ያዘ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ወደ ናኮ​ንም አው​ድማ ደረሱ፤ ዖዛም በሬ​ዎቹ አነ​ቃ​ን​ቀ​ዋት ነበ​ርና ይይ​ዛት ዘንድ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት እጁን ዘረጋ፤ አስ​ተ​ካ​ከ​ላ​ትም። ሲይ​ዛ​ትም በሬው ወጋው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ወደ ናኮንም አውድማ በደረሱ ጊዜ በሬዎቹ ይፋንኑ ነበርና ዖዛ እጁን ዘርግቶ የእግዚአብሔርን ታቦት ያዘ።

Ver Capítulo



2 ሳሙኤል 6:6
5 Referencias Cruzadas  

ከዮርዳኖስ በስተምሥራቅ “አጣድ” ተብላ ወደምትጠራው አውድማ ደረሱ፤ እዚያም ድምፃቸውን ከፍ አድርገው በመጮኽ አለቀሱ፤ ዮሴፍም እዚያ ሰባት ቀን ሙሉ የሐዘን ውሎ አደረገ።


ወደ ኪዶንም አውድማ በደረሱ ጊዜ ሠረገላውን የሚጐትቱት በሬዎች ሲፋንኑ አደናቀፋቸው፤ ዑዛም እጆቹን ዘርግቶ የቃል ኪዳኑን ታቦት በመደገፍ ያዘ፤


ከሰፈር በሚነሡበትም ጊዜ አሮንና ልጆቹ ንዋያተ ቅድሳቱንና የእነርሱንም መገልገያ ዕቃዎች ሁሉ ከሸፈኑ በኋላ የቀዓት ልጆች መጥተው ይሸከሙአቸው፤ ነገር ግን እንዳይሞቱ ንዋያተ ቅድሳቱን መንካት አይገባቸውም፤ እንግዲህ የመገናኛው ድንኳን በሚነሣበት ጊዜ ሁሉ የቀዓት ልጆች ኀላፊነት ይህ ነው።


“የቀዓትን ልጆች ከሌዋውያን ነገድ መካከል ተቀሥፈው እንዲጠፉ አታድርጉ፤