ንጉሥ ሰሎሞንና መላው የእስራኤል ሕዝብ በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት ተሰበሰቡ፤ ከብዛቱም የተነሣ ሊቈጠር የማይቻል ብዙ በግና የቀንድ ከብት መሥዋዕት አድርገው አቀረቡ።
2 ሳሙኤል 6:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙት ሰዎች ስድስት እርምጃ በተራመዱ ቊጥር ዳዊት እንደገና እያስቆመ አንድ ወይፈንና አንድ የሰባ ፍሪዳ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ያቀርብ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነዚያ የእግዚአብሔርን ታቦት ተሸክመው የነበሩት ሰዎች ስድስት ርምጃ በሄዱ ቍጥር፣ አንድ በሬና አንድ የሠባ ጥጃ ይሠዋ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነዚያ የጌታን ታቦት ተሸክመው የነበሩት ሰዎች ስድስት ርምጃ በሄዱ ቍጥር፥ በሬና የሰባ ፍሪዳ ይሠዋ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእርሱም ጋር የእግዚአብሔርን ታቦት የተሸከሙ ሰባት መሰንቆ የሚመቱ ክፍሎች ነበሩ። በሬዎችንና በጎችን ይሠዉ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔርንም ታቦት የተሸከሙ ስድስት እርምጃ በሄዱ ጊዜ አንድ በሬና አንድ ፍሪዳ ሠዋ። |
ንጉሥ ሰሎሞንና መላው የእስራኤል ሕዝብ በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት ተሰበሰቡ፤ ከብዛቱም የተነሣ ሊቈጠር የማይቻል ብዙ በግና የቀንድ ከብት መሥዋዕት አድርገው አቀረቡ።
ከዚህም በኋላ ዳዊት እግዚአብሔር ለዘለዓለም እርሱን እንዲያገለግሉና የቃል ኪዳኑንም ታቦት እንዲሸከሙ የመረጣቸው እነርሱን ስለ ሆነ “የቃል ኪዳኑን ታቦት መሸከም የሚገባቸው ሌዋውያን ብቻ ናቸው” አለ።
ንጉሥ ሰሎሞንና ሕዝቡ ሁሉ በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት ለፊት ተሰበሰቡ፤ ከዚህም በኋላ ከብዛታቸው የተነሣ ሊቈጠሩ የማይችሉ እጅግ ብዙ በጎችንና የቀንድ ከብቶችን መሥዋዕት አድርገው አቀረቡ።
ከሰፈር በሚነሡበትም ጊዜ አሮንና ልጆቹ ንዋያተ ቅድሳቱንና የእነርሱንም መገልገያ ዕቃዎች ሁሉ ከሸፈኑ በኋላ የቀዓት ልጆች መጥተው ይሸከሙአቸው፤ ነገር ግን እንዳይሞቱ ንዋያተ ቅድሳቱን መንካት አይገባቸውም፤ እንግዲህ የመገናኛው ድንኳን በሚነሣበት ጊዜ ሁሉ የቀዓት ልጆች ኀላፊነት ይህ ነው።
በእነርሱ ኀላፊነት የሚጠበቁት ንዋያተ ቅድሳት በትከሻቸው የሚሸከሙአቸው ስለ ሆኑ ሙሴ ለቀዓታውያን ሠረገሎችንም ሆነ በሬዎችን አልሰጣቸውም።
“ንጉሡ ሌሎች አገልጋዮችን እንደገና እንዲህ ሲል ላከ፤ ‘ወደ ተጠሩት ሰዎች ሂዱና፦ እነሆ፥ የሠርግ ድግሴን አዘጋጅቻለሁ፤ ሰንጋዎቼና የሰቡት ፍሪዳዎቼ ታርደዋል፤ ሁሉም ነገር ተዘጋጅቶአል፤ ስለዚህ ወደ ሠርጉ ግብዣ ኑ!’ ብላችሁ ንገሩአቸው።
የሚከተለውን ትእዛዝ ሰጡ፦ “የሌዊ ዘር የሆኑት ካህናት የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት ተሸክመው ሲነሡ በምታዩበት ጊዜ፥ ሰፈሩን ለቃችሁ እነርሱን ተከተሉ።