ሌላው ዝነኛ ወታደር የቃብጽኤል ተወላጅ የነበረው የዮዳሄ ልጅ በናያ ነበር፤ እርሱም ሁለት የታወቁ ሞአባውያን ወታደሮችን ከመግደሉም ሌላ ብዙ የጀግንነት ሥራ ፈጽሞአል፤ አንድ ጊዜ በምድር ላይ ዐመዳይ በወረደበት ቀን ወደ አንድ ዋሻ ወርዶ አንበሳ ገደለ፤
2 ሳሙኤል 23:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም ጦር ይዞ የነበረውን አንድ ኀያል ግብጻዊ ገድሎአል፤ ይኸውም በናያ በእጁ ከበትር በስተቀር ሌላ የጦር መሣሪያ ሳይዝ ወደ ግብጻዊው ቀርቦ የገዛ ጦሩን በመቀማት በዚያው ጦር ግብጻዊውን ገደለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደግሞም አንድ ግዙፍ ግብጻዊ ገድሏል፤ ግብጻዊው በእጁ ጦር የያዘ ቢሆንም፣ በናያስ ግን ሊገጥመው በትር ይዞ ወደ እርሱ ሄደ፤ ከግብጻዊውም እጅ ጦሩን ነጥቆ በገዛ ጦሩ ገደለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንድ ማራኪ ግብፃዊንም ገድሎአል፤ ግብፃዊው በእጁ ጦር ይዞ፥ በናያ ግን ሊገጥመው በትር ይዞ ነበር ወደ እርሱ የሄደው፤ ከግብፃዊውም እጅ የገዛ ጦሩን በመንጠቅ ገደለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም ልዩ የሆነውን ግብፃዊ ሰው ገደለ፤ ግብፃዊውም በእጁ ዛቢያው እንደ ድልድይ ዕንጨት የሆነ ጦር ነበረው፤ በናያስ ግን በትር ይዞ ወደ እርሱ ወረደ፤ ከግብፃዊውም እጅ ጦሩን ነጥቆ በገዛ ጦሩ ገደለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ረጅሙንም ግብጻዊ ሰው ገደለ፥ ግብጻዊው በእጁ ጦር ነበረው፥ በናያስ ግን በትር ይዞ ወደ እርሱ ወረደ፥ ከግብጻዊውም እጅ ጦሩን ነቅሎ በገዛ ጦሩ ገደለው። |
ሌላው ዝነኛ ወታደር የቃብጽኤል ተወላጅ የነበረው የዮዳሄ ልጅ በናያ ነበር፤ እርሱም ሁለት የታወቁ ሞአባውያን ወታደሮችን ከመግደሉም ሌላ ብዙ የጀግንነት ሥራ ፈጽሞአል፤ አንድ ጊዜ በምድር ላይ ዐመዳይ በወረደበት ቀን ወደ አንድ ዋሻ ወርዶ አንበሳ ገደለ፤
እንዲሁም በጣም ትልቅ ጦር ይዞ የነበረውን፥ ቁመቱ ከሁለት ሜትር በላይ የሆነውን፥ አንድ ግዙፍ ግብጻዊ ገድሎአል፤ ይኸውም በናያ በእጁ ከበትር በስተቀር ሌላ የጦር መሣሪያ ሳይዝ ወደ ግብጻዊው ቀርቦ ከመታው በኋላ ግብጻዊው ይዞት የነበረውን የሸማኔ መጠቅለያ የሚመስለውን የገዛ ጦሩን ቀምቶ ገደለው።
ወደ እርሱም ሮጦ በመሄድ በላዩ ላይ ቆመ፤ የጎልያድንም ሰይፍ ከሰገባው በመምዘዝ ራሱን ቈረጠው። ፍልስጥኤማውያንም የእነርሱ ዝነኛ ተዋጊ ጎልያድ መገደሉን ባዩ ጊዜ ሸሹ።