ዳዊት በከተማይቱ ውስጣዊና ውጫዊ በሮች መካከል ባለው ግልጥ ቦታ ተቀምጦ ነበር፤ ጠባቂው በቅጥሩ በኩል ወደ ማማው ወጥቶ ስለ ነበር ቀና ብሎ ሲመለከት አንድ ሰው ብቻውን እየሮጠ ሲመጣ አየ፤
2 ሳሙኤል 18:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዘበኛውም ድምፁንም በማሰማት ያየውን ለንጉሡ ነገረው፤ ንጉሡም “ብቻውን ከሆነ መልካም ወሬ ይዞ የመጣ መሆን አለበት” አለ፤ ያም ሯጭ ሰው እየቀረበ መጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጠባቂውም ተጣራና ይህንኑ ለንጉሡ ነገረው። ንጉሡም፣ “ብቻውን ከሆነ መልካም ወሬ ይዞ የመጣ መሆን አለበት” አለ። ሰውየውም እየቀረበ መጣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጠባቂው ተጣራና ይህንኑ ለንጉሡ ነገረው፤ ንጉሡም፥ “ብቻውን ከሆነ መልካም ወሬ ይዞ ይሆናል” አለ። ሰውየውም እየቀረበ መጣ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዘበኛውም ለንጉሡ ሊነግረው ጮኸ። ንጉሡም፥ “ብቻውን እንደ ሆነ በአፉ ወሬ ይኖራል” አለ። እርሱም ፈጥኖ ቀረበ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዘበኛውም ለንጉሡ ሊነግረው ጮኸ። ንጉሡም፦ ብቻውን እንደሆነ በአፉ ወሬ ይኖራል አለ። |
ዳዊት በከተማይቱ ውስጣዊና ውጫዊ በሮች መካከል ባለው ግልጥ ቦታ ተቀምጦ ነበር፤ ጠባቂው በቅጥሩ በኩል ወደ ማማው ወጥቶ ስለ ነበር ቀና ብሎ ሲመለከት አንድ ሰው ብቻውን እየሮጠ ሲመጣ አየ፤
ዘበኛውም እንደገና አንድ ሌላ ሰው እየሮጠ ሲመጣ አይቶ፥ የቅጽር በር ጠባቂውን በመጣራት “ተመልከት! ሌላም አንድ ሰው እየሮጠ በመምጣት ላይ ነው!” አለው። ንጉሡም “ይህኛውም መልካም ወሬ ይዞ የሚመጣ ሊሆን ይችላል” ሲል መለሰ።