በዚህ አገር የኖርከውም ለአጭር ጊዜ ነው፤ ታዲያ አንተ ከእኔ ጋር የምትንከራተተው ስለምንድን ነው? እኔ የት እንደምሄድ እንኳ አላውቅም፤ ስለዚህ የአገርህን ሰዎች ይዘህ ተመለስ፤ እግዚአብሔር ቸርነቱንና እውነተኛነቱን ይግለጥልህ።”
2 ሳሙኤል 15:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሡም ኢታይ ተብሎ የሚጠራውን የጌት ሰው እንዲህ አለው፤ “ከእኛ ጋር ለምን ትሄዳለህ? ተመልሰህ ከአዲሱ ንጉሥ ጋር ቈይ፤ አንተ ከአገርህ ወጥተህ በመጻተኛነት እዚህ የምትኖር የውጪ አገር ሰው ነህ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሡም ጋታዊውን ኢታይን እንዲህ አለው፤ “ከእኛ ጋራ የመጣኸው ለምንድን ነው? ተመለስና ከንጉሡ ከአቤሴሎም ጋራ ተቀመጥ፤ አንተ ለራስህ ከአገርህ ተወስደህ የመጣህ እንግዳ ነህ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሡም የጌታዊውን ሰው ኢታይን እንዲህ አለው፤ “አንተም ከእኛ ጋር አብረህ የመጣኸው ለምንድን ነው? ተመለስና ከንጉሥ አቤሴሎም ጋር ተቀመጥ፤ አንተ እኮ ከስፍራህ በግዞት የመጣህ መጻተኛ ነህ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡም ጌታዊውን ኤቲን፥ “ከእኛ ጋር ለምን መጣህ? አንተ ከስፍራህ የመጣህ ስደተኛና እንግዳ ነህና ተመለስ፤ ከንጉሡም ጋር ተቀመጥ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም የጌት ሰው ኢታይን፦ ከእኛ ጋር ለምን መጣህ? አንተ ከስፍራህ የመጣህ እንግዳና ስደተኛ ነህና ተመለስ፥ ከንጉሡም ጋር ተቀመጥ። |
በዚህ አገር የኖርከውም ለአጭር ጊዜ ነው፤ ታዲያ አንተ ከእኔ ጋር የምትንከራተተው ስለምንድን ነው? እኔ የት እንደምሄድ እንኳ አላውቅም፤ ስለዚህ የአገርህን ሰዎች ይዘህ ተመለስ፤ እግዚአብሔር ቸርነቱንና እውነተኛነቱን ይግለጥልህ።”
ከዚህም በኋላ ሦስት ክፍል አድርጎ ላካቸው፤ ኢዮአብን የሢሶው፥ አቢሳይ የሢሶው፥ እንዲሁም የጋት ተወላጅ የሆነው ኢታይ የሢሶው አዛዦች ሆኑ፤ ንጉሡም ተከታዮቹን “እኔም ራሴ አብሬአችሁ እሄዳለሁ” አላቸው።