እግዚአብሔርም ልጁ ምርር ብሎ ሲያለቅስ ሰማ፤ የእግዚአብሔርም መልአክ ከሰማይ አጋርን “አጋር ሆይ፤ የምትጨነቂበት ነገር ምንድን ነው? እግዚአብሔር የልጁን ለቅሶ ሰምቶአልና አይዞሽ አትፍሪ፤
2 ሳሙኤል 14:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሡም “ምን ችግር አጋጠመሽ?” አላት፤ እርስዋም እንዲህ ስትል መለሰች፦ “እኔ ባሌ የሞተብኝ መበለት ሴት ነኝ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሡም፣ “ችግርሽ ምንድን ነው?” ብሎ ጠየቃት። እርሷም እንዲህ አለች፤ “እኔ በርግጥ ባሌ የሞተብኝ መበለት ነኝ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሡም፥ “ችግርሽ ምንድነው?” ብሎ ጠየቃት። እርሷም እንዲህ አለች፤ “እኔ በእርግጥ ባሌ የሞተብኝ መበለት ነኝ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡም፥ “ምን ሆነሻል?” አላት። እርስዋም አለች፥ “በእውነት እኔ ባሌ የሞተብኝ ባልቴት ሴት ነኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም፦ ምን ሆነሻል? አላት። እርስዋም መልሳ አለች፦ ክ በእውነት እኔ ባሌ የሞተብኝ ባልቴት ሴት ነኝ። |
እግዚአብሔርም ልጁ ምርር ብሎ ሲያለቅስ ሰማ፤ የእግዚአብሔርም መልአክ ከሰማይ አጋርን “አጋር ሆይ፤ የምትጨነቂበት ነገር ምንድን ነው? እግዚአብሔር የልጁን ለቅሶ ሰምቶአልና አይዞሽ አትፍሪ፤
ንጉሥ ሆይ! እኔ አገልጋይህ ሁለት ወንዶች ልጆች ነበሩኝ፤ አንድ ቀን ገላጋይ በሌለበት ስፍራ ሁለቱ ልጆቼ እርስ በርሳቸው ተጣሉ፤ አንዱ ሌላውን ገደለው፤