2 ሳሙኤል 14:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የራሱ ጠጒር እጅግ ብዙ ነበር፤ ስለሚረዝምበትና ስለሚከብደው በዓመት አንድ ጊዜ ይቈርጠው ነበር፤ የጠጒሩም ክብደት በቤተ መንግሥት ሚዛን ሲለካ ከሁለት ኪሎ በላይ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የራስ ጠጕሩ ሲከብደው በዓመት አንድ ጊዜ ይቈርጠው ነበር፤ የተቈረጠውን በሚመዝነው ጊዜ ክብደቱ በንጉሥ ሚዛን ሁለት መቶ ሰቅል ይሆን ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የራስ ጠጉሩ ሲከብደው በዓመት አንድ ጊዜ ይቆርጠው ነበር፤ የተቆረጠውን በሚመዝነው ጊዜ ክብደቱ በቤተ መንግሥት ሚዛን ሁለት መቶ ሰቅል ይሆን ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቀድሞ በመጀመሪያ ዘመን ጠጕሩ ይከብደው ነበርና በዓመት አንድ ጊዜ ይቈረጠው ነበር፤ ሲቈረጥም የራሱ ጠጕር በንጉሥ ሚዛን ሁለት መቶ ሰቅል ያህል ይመዝን ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጠጕሩም ይከብደው ነበርና በዓመት አንድ ጊዜ ይቆርጠው ነበር፥ ሲቆርጥም የራሱ ጠጕር በንጉሥ ሚዛን ሁለት መቶ ሰቅል ያህል ይመዘን ነበር። |
በድንገት፥ አቤሴሎም ከዳዊት ተከታዮች ጥቂቱን አገኘ፤ አቤሴሎም በዚያን ጊዜ በበቅሎ ላይ ተቀምጦ ይጋልብ ስለ ነበር በቅሎዋ በአንድ ትልቅ የወርካ ዛፍ ሥር ስታልፍ ሳለ የዛፉ ቅርንጫፍ የአቤሴሎምን ራስ ጠጒር ያዘበት፤ በቅሎዋም በእግሮቹ መኻል ሾልካ ስትሄድ አቤሴሎም በዐየር ላይ ተንጠልጥሎ ቀረ።
ስለዚህ በሽቶ ፈንታ ግማት፥ በጥሩ መታጠቂያ ፈንታ ገመድ፥ በጐፈሬ ፈንታ ቡሃነት፥ በመጐናጸፊያ ፈንታ ማቅ፥ በውበትም ፈንታ ጠባሳ መሆን ይመጣባቸዋል!