እርስዋም “አይሆንም! እኔን እንደዚህ አድርገህ ብታባርረኝ አሁን ከፈጸምከው በደል ይልቅ የከፋ ኃጢአት ትፈጽማለህ!” አለችው። አምኖን ግን ሊያዳምጣት አልፈቀደም፤
2 ሳሙኤል 13:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የግል አገልጋዩንም ጠርቶ “ይህችን ሴት ከፊቴ ወዲያ አስወግድልኝ! እርስዋንም ወደ ውጪ አስወጥተህ በሩን ዝጋ!” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በግል የሚያገለግለውን ወጣት ጠርቶ፣ “ይህችን ሴት ከዚህ አስወጣና በሩን ዝጋባት” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወጣት አገልጋዩንም ጠርቶ፥ “ይህቺን ሴት ከፊቴ አስወጣና በሩን ዝጋባት” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በበር ቁሞ የሚያገለግለውንም ብላቴና ጠርቶ፥ “ይህችን ሴት ከፊቴ አስወጥተህ በሩን ዝጋባት” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሚያገለግለውንም ብላቴና ጠርቶ፦ ይህችን ሴት ከፊቴ አስወጥተህ በሩን ዝጋባት አለው። |
እርስዋም “አይሆንም! እኔን እንደዚህ አድርገህ ብታባርረኝ አሁን ከፈጸምከው በደል ይልቅ የከፋ ኃጢአት ትፈጽማለህ!” አለችው። አምኖን ግን ሊያዳምጣት አልፈቀደም፤
ትዕማርም የአምኖን አሽከር ከቤት አስወጥቶ በሩን ዘጋባት፤ በዚያን ዘመን ያላገቡ የነገሥታት ልጆች ይለብሱት የነበረውን እጅጌ ረዥም የነበረ መጐናጸፊያ ለብሳ ነበር፤ እርስዋም በራስዋ ላይ አመድ ነስንሳ ለብሳው የነበረውን መጐናጸፊያ ቀዳ እጅዋን በራስዋ ላይ በመጫን ድምፅዋን ከፍ አድርጋ እያለቀሰች ሄደች።