2 ሳሙኤል 13:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በምታቀርብለትም ጊዜ አፈፍ በማድረግ ይዞ “እኅቴ ሆይ! አብረን እንተኛ!” አላት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ምግቡን ስታቀርብለት አፈፍ አድርጎ ያዛትና፣ “እኅቴ ነዪ ዐብረን እንተኛ” አላት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ምግቡን ስታቀርብለት አፈፍ አድርጎ ያዛትና፥ “እህቴ ነዪ አብረን እንተኛ” አላት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይበላም ዘንድ መብሉን አቀረበችለት። እርሱም ያዛትና፥ “እኅቴ ሆይ፥ ነዪ ከእኔ ጋር ተኚ” አላት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መብሉንም ባቀረበች ጊዜ ያዛትና፦ እኅቴ ሆይ፥ ነዪ ከእኔም ጋር ተኚ አላት። |
ከዚያም በኋላ አምኖን ትዕማርን “ታጐርሺኝ ዘንድ ምግቡን ይዘሽ ወደ አልጋዬ አምጪው” አላት፤ ስለዚህም ትዕማር ምግቡን ወደ ወንድምዋ ወደ አምኖን አመጣችው።