2 ሳሙኤል 13:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም በኋላ አምኖን ትዕማርን “ታጐርሺኝ ዘንድ ምግቡን ይዘሽ ወደ አልጋዬ አምጪው” አላት፤ ስለዚህም ትዕማር ምግቡን ወደ ወንድምዋ ወደ አምኖን አመጣችው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም አምኖን ትዕማርን፣ “እንድታጐርሺኝ ምግቡን እዚሁ መኝታ ክፍሌ አምጪልኝ” አላት። ትዕማርም ያዘጋጀችውን እንጀራ ይዛ ወንድሟ አምኖን ወዳለበት መኝታ ክፍል ገባች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም አምኖን ትዕማርን፥ “እንድታጐርሺኝ ምግቡን እዚሁ መኝታ ክፍሌ አምጪልኝ” አላት። ትዕማርም ያዘጋጀችውን እንጀራ ይዛ ወንድሟ አምኖን ወዳለበት መኝታ ክፍል ገባች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምኖንም ትዕማርን፥ “በእጅሽ እበላ ዘንድ መብሉን ወደ እልፍኙ አግቢው” አላት፤ ትዕማርም የሠራችውን እንጎቻ ወስዳ ወንድምዋ አምኖን ወዳለበት እልፍኝ አገባችው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምኖንም ትዕማርን፦ ከእጅሽ እበላ ዘንድ መብሉን ወደ እልፍኙ አግቢው አላት፥ ትዕማርም የሠራችውን እንጎቻ ወስዳ ወንድምዋ አምኖን ወዳለበት እልፍኝ አገባችው። |
የጋገረችውንም እንጀራ ከምጣዱ አውጥታ እንዲበላ አቀረበችለት፤ እርሱ ግን መመገቡን እምቢ ብሎ “ሰዎቹን ሁሉ አስወጡልኝ” አለ፤ ሁሉም ወጡ፤