La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ሳሙኤል 10:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ኢዮአብ የጠላት ሠራዊት ከፊትና ከኋላ በኩል አደጋ እንደሚጥልበት ተመለከተ፤ ስለዚህ ከእስራኤል ወታደሮች ጀግኖች የሆኑትን መርጦ በሶርያውያን ፊት ለፊት አመች በሆነ ስፍራ መደባቸው፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ኢዮአብም ከፊትና ከኋላው ጦር እንደ ከበበው ባየ ጊዜ፣ በእስራኤል ጀግንነታቸው ከታወቀው ጥቂቶቹን መርጦ በሶርያውያን ግንባር አሰለፋቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ኢዮአብም ከፊትና ከኋላው ጦር እንደ ከበበው ባየ ጊዜ፥ በእስራኤል ጀግንነታቸው ከታወቀው ጥቂቶቹን መርጦ በሶርያውያን ግንባር አሰለፋቸው።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ኢዮ​አ​ብም በፊ​ትና በኋላ ሰልፍ እንደ ከበ​በው ባየ ጊዜ ከእ​ስ​ራ​ኤል ጐል​ማ​ሶ​ችን ሁሉ መረጠ፤ በሶ​ር​ያ​ው​ያ​ንም ፊት አሰ​ለ​ፋ​ቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ኢዮአብም በፊትና በኋላ ሰልፍ እንደ ከበበው ባየ ጊዜ ከእስራኤል ምርጥ ምርጦቹን ሁሉ መረጠ፥ በሶርያውያንም ፊት ለሰልፍ አኖራቸው።

Ver Capítulo



2 ሳሙኤል 10:9
6 Referencias Cruzadas  

ከሠራዊቱ ቀሪውን ክፍል በወንድሙ በአቢሳይ ትእዛዝ ሥር አደረገ፤ አቢሳይም እነርሱን በዐሞናውያን ፊት ለፊት አሰለፋቸው፤


ዐሞናውያን ተሰልፈው ወጥተው የእነርሱ ዋና ከተማቸው በሆነችው በራባ መግቢያ በር አጠገብ ስፍራቸውን ያዙ፤ ሌሎቹ ሶርያውያን፥ ከጦብና ከማዕካ የመጡት ጦረኞች በአንድ ሜዳማ ቦታ ስፍራቸውን ያዙ።


ከዚህም በኋላ ሦስት ክፍል አድርጎ ላካቸው፤ ኢዮአብን የሢሶው፥ አቢሳይ የሢሶው፥ እንዲሁም የጋት ተወላጅ የሆነው ኢታይ የሢሶው አዛዦች ሆኑ፤ ንጉሡም ተከታዮቹን “እኔም ራሴ አብሬአችሁ እሄዳለሁ” አላቸው።


የይሁዳ ሕዝብም ዙሪያውን ተመልክቶ መከበቡን ባየ ጊዜ እንዲረዳው ወደ እግዚአብሔር ጮኸ፤ ካህናቱም እምቢልታ ነፉ፤