2 ሳሙኤል 10:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጾባው ሀዳድዔዜር ከኤፍራጥስ ወንዝ በስተ ምሥራቅ ወደሚገኙት ሶርያውያን መልእክት ላከ፤ እነርሱም የሀዳድዔዜር የሠራዊት አለቃ በሆነው በሾባክ መሪነት ወደ ሔላም መጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አድርአዛር መልክተኞችን ሰድዶ ከወንዙ ማዶ ያሉትን ሶርያውያን አስመጣ፤ እነርሱም በአድርአዛር ሰራዊት አዛዥ በሶባክ መሪነት ወደ ኤላም ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሀዳድዔዜር መልክተኞችን ሰዶ ከወንዙ ማዶ ያሉትን ሶርያውያን አስመጣ፤ እነርሱም በሀዳድዔዜር ሠራዊት አዛዥ በሾባክ መሪነት ወደ ሔላም ሄዱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አድርአዛርም ልኮ በካላማቅ ወንዝ ማዶ የነበሩትን ሶርያውያን ሰበሰባቸው፤ ወደ ኤላምም መጡ፤ የአድርአዛርም ሠራዊት አለቃ ሶቤቅ በፊታቸው ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አድርአዛርም ልኮ በወንዝ ማዶ የነበሩትን ሶርያውያን አመጣ፥ ወደ ኤላምም መጡ፥ የአድርአዛርም ሠራዊት አለቃ ሶባክ በፊታቸው ነበረ። |
ዳዊትም ይህን በሰማ ጊዜ የእስራኤላውያንን ወታደሮች ሁሉ በአንድነት አሰባስቦ የዮርዳኖስን ወንዝ ተሻገረ፤ ከዚያም ሶርያውያን ወደ ሰፈሩበት ወደ ሔላም ሄደ፤ ሶርያውያንም በሰልፍ ወጥተው በዳዊት ላይ ጦርነት ከፈቱ፤
እንደገናም እግዚአብሔር ረዞን ተብሎ የሚጠራውን የኤሊዓዳን ልጅ በሰሎሞን ላይ ጠላት አድርጎ አስነሣ፤ ረዞን የጾባ ንጉሥ ከነበረው ከጌታው ከሀዳድዔዜር ኮብልሎ፥
ቀጥሎም ንጉሥ ዳዊት በሶርያ አገር እስከ ሐማት ግዛት አጠገብ በምትገኘው በጾባ ንጉሥ በሀዳድዔዜር ላይ አደጋ ጣለ፤ ይህንንም ያደረገው ሀዳድዔዜር ከላይ በኩል በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ ያለውን ግዛት በቊጥጥሩ ሥር ለማድረግ ዘምቶ ስለ ነበር ነው፤
በደማስቆ ያሉ ሶርያውያን የጾባን ንጉሥ ሀዳድዔዜርን ለመርዳት ሠራዊት በላኩ ጊዜ ዳዊት በእነርሱም ላይ አደጋ ጥሎ ኻያ ሁለት ሺህ ወታደሮችን ገደለ፤
ሶርያውያን በእስራኤላውያን ድል እንደ ተመቱ በተገነዘቡ ጊዜ ከኤፍራጥስ በስተ ምሥራቅ በኩል ካሉት የሶርያ ግዛቶች ሠራዊት አስመጥተው በሾባክ አዛዥነት ሥር አደረጉአቸው፤ ሾባክ የጾባ ንጉሥ የሀዳድዔዜር የጦር አዛዥ ነበር፤