2 ነገሥት 6:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእነርሱም አንዱ ዛፍ በመቊረጥ ላይ ሳለ በድንገት መጥረቢያው ከዛቢያው ላይ ወድቆ ውሃ ውስጥ ገባ፤ እርሱም ድምፁን ከፍ አድርጎ በመጮኽ “ጌታዬ ሆይ! እንግዲህ ምን አደርጋለሁ? መጥረቢያው የተውሶ ነው!” ሲል ለኤልሳዕ ነገረው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእነርሱም አንዱ ዛፍ እየቈረጠ ሳለ፣ መጥረቢያው በርሮ ከውሃው ውስጥ ወደቀ፤ እርሱም፣ “ወየው ጌታዬ፤ የተውሶ መጥረቢያ እኮ ነው!” ብሎ ጮኸ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእነርሱም አንዱ ዛፍ በመቁረጥ ላይ ሳለ በድንገት መጥረቢያው ከዛቢያው ላይ ወድቆ ውሃ ውስጥ ገባ፤ እርሱም ድምፁን ከፍ አድርጎ በመጮኽ “ጌታዬ ሆይ! እንግዲህ ምን አደርጋለሁ? መጥረቢያው የተውሶ ነው!” ሲል ለኤልሳዕ ነገረው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእነርሱም አንዱ ዛፉን ሲቈርጥ የምሳሩ ብረት ወልቆ ወደ ውኃው ውስጥ ወደቀ፤ እርሱም፥ “ጌታዬ ሆይ፥ ወየው! ወየው! የተዋስሁት ነበር” ብሎ ጮኸ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእነርሱም አንዱ ምሰሶውን ሲቆርጥ የምሳሩ ብረት ወደ ውሃው ውስጥ ወደቀ፤ እርሱም “ጌታዬ ሆይ! ወየው! ወየው! የተዋስሁት ነበረ፤” ብሎ ጮኸ። |
እርስዋም ተመልሳ ወደ ነቢዩ ኤልሳዕ ሄደች፤ እርሱም “እንግዲህ ዘይቱን ሸጠሽ ዕዳሽን በሙሉ ክፈይ፤ ለአንቺና ለልጆችሽ መተዳደሪያ የሚሆንም ብዙ ገንዘብ ይተርፍሻል” አላት።
በማግስቱም ማለዳ የኤልሳዕ አገልጋይ ከመኝታው ተነሥቶ፥ ከቤት ሲወጣ በፈረሶችና በሠረገሎች የታጀቡ የሶርያ ወታደሮች ከተማይቱን መክበባቸውን አየ፤ ወደ ኤልሳዕም ተመልሶ ድምፁን ከፍ በማድረግ “ጌታዬ ወዮ! ምን ማድረግ ይሻለናል?” ሲል ጠየቀው።
ኤልሳዕም “በየት በኩል ነው የወደቀው?” ሲል ጠየቀው። ሰውየውም መጥረቢያው የወደቀበትን ስፍራ ባሳየው ጊዜ እርሱ አንድ እንጨት ቈርጦ ወደ ውሃው ውስጥ በመጣል መጥረቢያው እንዲንሳፈፍ አደረገው፤
በደን መካከል የሚገኝ ዛፍ በመጥረቢያ ተቈርጦ እንደሚወድቅ እነርሱንም እግዚአብሔር ይቈራርጣቸዋል፤ ምርጥ የሆኑ የሊባኖስ ዛፎችም ተቈርጠው እንደሚወድቁ እነርሱም በኀያሉ አምላክ ተቈርጠው ይወድቃሉ።
ሥቃይዋንም በመፍራት በሩቅ ቆመው “አንቺ ታላቂቱ ከተማ፥ አንቺ ብርቱይቱ ከተማ ባቢሎን ሆይ! ፍርድሽ በአንድ ሰዓት ውስጥ ስለ መጣ፥ ወዮልሽ! ወዮልሽ!” ይላሉ።
“ቀጭን ልብስና ሐምራዊ ልብስ ቀይ ልብስም ትለብስ የነበረች፥ በወርቅና በከበረ ድንጋይ በዕንቊም ታሸበርቅ የነበረች፤ ታላቂቱ ከተማ ወዮላት! ወዮላት!
በራሳቸው ላይ አቧራ ነሰነሱ፤ እያለቀሱና እያዘኑም እንዲህ እያሉ ይጮኻሉ፤ “በባሕር ላይ መርከቦች ያላቸው ሁሉ በእርስዋ ሀብት ሀብታሞች የሆኑ፥ ያቺ ታላቅ ከተማ በአንድ ሰዓት ውስጥ ስለ ወደመች ወዮላት! ወዮላት!”