2 ነገሥት 4:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርስዋም ተመልሳ ወደ ነቢዩ ኤልሳዕ ሄደች፤ እርሱም “እንግዲህ ዘይቱን ሸጠሽ ዕዳሽን በሙሉ ክፈይ፤ ለአንቺና ለልጆችሽ መተዳደሪያ የሚሆንም ብዙ ገንዘብ ይተርፍሻል” አላት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሷም ሄዳ ይህንኑ ለእግዚአብሔር ሰው ነገረችው። እርሱም፣ “ሄደሽ ዘይቱን በመሸጥ ዕዳሽን ክፈይ፤ የተረፈውም ለአንቺና ለልጆችሽ መተዳደሪያ ይሁን” አላት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሷም ተመልሳ ወደ ነቢዩ ኤልሳዕ ሄደች፤ እርሱም “እንግዲህ ዘይቱን ሸጠሽ ዕዳሽን በሙሉ ክፈይ፤ ለአንቺና ለልጆችሽ መተዳደሪያ የሚሆንም ብዙ ገንዘብ ይተርፍሻል” አላት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መጥታም ለእግዚአብሔር ሰው ነገረችው፤ እርሱም፥ “ሄደሽ ዘይቱን ሽጭ ዕዳሽንም ክፈዪ፤ በተረፈውም ዘይት የአንቺንና የልጆችሽን ሰውነት አድኚ” አላት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መጥታም ለእግዚአብሔር ሰው ነገረችው፤ እርሱም “ሄደሽ ዘይቱን ሽጪ፤ ለባለዕዳውም ክፈይ፤ አንቺና ልጆችሽም ከተረፈው ተመገቡ፤” አለ። |
አእምሮአችሁ በእነዚህ ከሁሉ በሚበልጡና በሚያስመሰግኑ መልካም ነገሮች የተመላ ይሁን፤ በመጨረሻም ወንድሞች ሆይ! እውነተኛ፥ ክቡር፥ ትክክለኛ፥ ንጹሕ፥ አስደሳችና ምስጉን የሆኑ ነገሮችን ሁሉ አስቡ።