2 ነገሥት 24:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በከበባውም ጊዜ ናቡከደነፆር ራሱ ወደ ኢየሩሳሌም መጣ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጦር አለቆቹ ከበባ በሚያደርጉበትም ሰዓት ንጉሥ ናቡከደነፆር ራሱ ወደ ከተማዪቱ መጣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በከበባውም ጊዜ ናቡከደነፆር ራሱ ወደ ኢየሩሳሌም መጣ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆርም ወደ ከተማዪቱ መጣ። ሠራዊቱም ከበቡአት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባሪያዎቹም በከበቡአት ጊዜ የባቢሎን ንጉሥ ናብከደነዖር ወደ ከተማይቱ ወጣ። |
ንጉሥ ኢኮንያን ከእናቱ፥ ከልዑላን መሳፍንቱ፥ ከጦር አዛዦቹና ባለሟሎቹ ከሆኑት ባለሥልጣኖች ጋር ቀርቦ ለባቢሎናውያን እጁን ሰጠ፤ ናቡከደነፆር በነገሠ በስምንተኛው ዓመት ኢኮንያንን እስረኛ አድርጎ ያዘው፤
ይህም የሚሆነው ንጉሡ የእናንተን አገር ወደምትመስል ምድር ወስዶ እስከሚያሰፍራችሁ ድረስ ነው፤ በዚያችም ምድር የወይን ጠጅ የሚገኝባቸው የወይን ተክል ቦታዎችና በቂ የእንጀራ እህል የሚመረትባቸው እርሻዎች አሉ፤
“የምሳሌውን ትርጒም ያውቁ እንደ ሆነ እስቲ እነዚህን ዐመፀኞች ጠይቃቸው፤ የባቢሎን ንጉሥ ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ንጉሡንና መሳፍንቱን ወደ ባቢሎን የወሰዳቸው መሆኑን ንገራቸው፤