2 ዜና መዋዕል 6:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሆኖም ለስሜ መጠሪያ እንዲሆን ቤተ መቅደስን የሚሠራልኝ ከአብራክህ የተገኘ የአንተው የራስህ ልጅ እንጂ አንተ አይደለህም’ አለው።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሁን እንጂ ቤተ መቅደሱን የምትሠራው አንተ አይደለህም፤ ለስሜ ቤተ መቅደስ የሚሠራልኝ ከአብራክህ የሚከፈለው፣ የገዛ ልጅህ ነው።’ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ከአብራክህ የተገኘው ልጅህ እርሱ ለስሜ ቤትን ይሠራል እንጂ ቤት የምትሠራልኝ አንተ አይደለህም።’ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ከወገብህ የሚወጣው ልጅህ እርሱ ለስሜ ቤትን ይሠራል እንጂ አንተ አትሠራልኝም አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ከወገብህ የሚወጣው ልጅህ እርሱ ለስሜ ቤትን ይሠራል እንጂ ቤት የምትሠራልኝ አንተ አይደለህም፤’ አለው። |
“እነሆ እግዚአብሔር የሰጠውን የተስፋ ቃል ፈጽሞአል፤ ስለዚህም እኔ በአባቴ እግር ተተክቼ የእስራኤል ንጉሥ ሆኜአለሁ፤ በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ስም ቤተ መቅደስ ሠርቼአለሁ፤