አሳ የይሁዳን ሰዎች እንዲህ አላቸው፤ “ግንቦችን፥ ቅጽሮችንና በብረት መወርወሪያ የሚዘጉ የቅጽር በሮችን በመሥራት፥ ከተሞቻችንን እንመሽግ፤ የአምላካችንን የእግዚአብሔርን ፈቃድ ስለ ፈጸምን፥ እነሆ፥ ምድሪቱ በቊጥጥራችን ሥር ናት፤ እግዚአብሔር ጠብቆናል፤ በሁሉም አቅጣጫ የሰላም ዋስትና ሰጥቶናል፤” ሕዝቡም ከተሞችን መሸገ፤ በለጸገም፤
2 ዜና መዋዕል 27:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም በይሁዳ ተራራማ ስፍራዎች ላይ ከተሞችን፥ ደን በበዛባቸው ስፍራዎችም ላይ ምሽጎችንና ቅጽሮችን ሠርቶ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በይሁዳ ኰረብቶች ላይ ከተሞችን፣ ደን በለበሱ ስፍራዎችም ምሽጎችንና ማማዎችን ሠራ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በተራራማውም በይሁዳ አገር ላይ ከተሞችን ሠራ፥ በዱር ስፍራዎችም አምባዎችንና ግንቦችን ሠራ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በተራራማውም በይሁዳ ሀገር ላይ ከተሞችን ሠራ፤ በዱር ስፍራዎችም አምባዎችንና ግንቦችን ሠራ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በተራራማውም በይሁዳ አገር ላይ ከተሞችን ሠራ፤ በዱር ስፍራዎችም አምባዎችንና ግንቦችን ሠራ። |
አሳ የይሁዳን ሰዎች እንዲህ አላቸው፤ “ግንቦችን፥ ቅጽሮችንና በብረት መወርወሪያ የሚዘጉ የቅጽር በሮችን በመሥራት፥ ከተሞቻችንን እንመሽግ፤ የአምላካችንን የእግዚአብሔርን ፈቃድ ስለ ፈጸምን፥ እነሆ፥ ምድሪቱ በቊጥጥራችን ሥር ናት፤ እግዚአብሔር ጠብቆናል፤ በሁሉም አቅጣጫ የሰላም ዋስትና ሰጥቶናል፤” ሕዝቡም ከተሞችን መሸገ፤ በለጸገም፤
ስለዚህ ኢዮሣፍጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ ይበልጥ ገናና እየሆነ ሄደ፤ በመላው ይሁዳ ምሽጎችንና፥ እጅግ የበዛ ስንቅና ትጥቅ የተከማቹባቸውን ከተማዎች ሠራ። በኢየሩሳሌምም የተለየ ችሎታ ያላቸውን ተዋጊዎች አኖረ፤
በዐሞን ንጉሥና በሠራዊቱ ላይ ጦርነት ከፍቶ ድል አድርጎአቸው ነበር፤ ዐሞናውያንንም በየዓመቱ ለሦስት ዓመት በተከታታይ ሦስት ሺህ አራት መቶ ኪሎ የሚመዝን ብር፥ አንድ ሚሊዮን ኪሎ የሚመዝን ስንዴና እንዲሁም አንድ ሚሊዮን ኪሎ የሚመዝን ገብስ እንዲገብሩለት አስገደዳቸው።