2 ዜና መዋዕል 13:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ አቢያ ኰረብታማ በሆነ በኤፍሬም አገር ወደሚገኘው ወደ ጸማራይም ተራራ ወጥቶ ቆመ፤ ድምፁን ከፍ በማድረግም ለኢዮርብዓምና ለእስራኤላውያን በሙሉ እንዲህ አለ፤ “እነሆ፥ አድምጡኝ! አዲሱ መደበኛ ትርጒም አብያ በኰረብታማው በኤፍሬም አገር በጽማራይም ተራራ ላይ ቆሞ፣ እንዲህ አለ፤ “ኢዮርብዓምና እስራኤል ሁሉ ስሙኝ! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አብያም በተራራማው በኤፍሬም አገር ባለው በጽማራይም ተራራ ላይ ቆሞ እንዲህ አለ፦ “ኢዮርብዓምና እስራኤል ሁሉ ሆይ! ስሙኝ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አብያም በኤፍሬም ተራራ ባለው በሳምሮን ተራራ ላይ ቆሞ እንዲህ አለ፥ “ኢዮርብዓምና እስራኤል ሁሉ ሆይ፥ ስሙኝ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አብያም በተራራማው በኤፍሬም አገር ባለው በጽማራይም ተራራ ላይ ቆሞ እንዲህ አለ“ኢዮርብዓምና እስራኤል ሁሉ ሆይ! ስሙኝ፤ |
ዐዛርያስም ከንጉሥ አሳ ጋር ለመገናኘት ሄዶ እንዲህ አለው፤ “ንጉሥ አሳ ሆይ! አድምጠኝ! እናንተም የይሁዳና የብንያም ሰዎች ሁሉ ስሙኝ! እናንተ ከእግዚአብሔር ጋር እስከ ሆናችሁ ድረስ እርሱም ከእናንተ ጋር ይሆናል፤ ከፈለጋችሁትም ታገኙታላችሁ፤ ብትተዉት ግን ይተዋችኋል፤
ኢዮአታም ይህን ነገር በሰማ ጊዜ ወደ ገሪዛን ተራራ ጫፍ ላይ ወጥቶ እንዲህ በማለት ወደ እነርሱ ጮኸ፤ “እናንተ የሴኬም ሰዎች! እኔን ብታዳምጡኝ እግዚአብሔርም እናንተን ያዳምጣችኋል።