እነዚህም ከግብጽ በስተ ምሥራቅ ካለው ከሺሆን ወንዝ ጀምሮ ወደ ሰሜን እስከ ኤክሮን ድንበር ድረስ ያለው ነው። ይህም በአጠቃላይ ከነዓን ተብሎ ይጠራል። እርሱም የአምስቱ የፍልስጥኤም ማለት የጋዛ፥ የአሽዶድ፥ የአስቀሎና፥ የጋትና የኤክሮን ነገሥታት ግዛት ነው። ሌሎች ያልተያዙ ደግሞ በደቡብ በኩል ያለው የአቢብ ግዛት ነው።
1 ሳሙኤል 6:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምስቱም የፍልስጥኤም ገዢዎች ይህን ሁሉ ሲመለከቱ ቈይተው በዚያው ቀን ወደ ዔቅሮን ተመለሱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዐምስቱ የፍልስጥኤም ገዦችም ይህን ሁሉ ካዩ በኋላ በዚያ ዕለት ወደ አቃሮን ተመለሱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አምስቱ የፍልስጥኤም ገዢዎችም ይህን ተመልክተው፥ በዚያው ዕለት ወደ ዔቅሮን ተመለሱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነዚያም የፍልስጥኤማውያን አምስቱ አለቆች አይተው በዚያው ቀን ወደ አስቀሎና ተመለሱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፍልስጥኤማውያንም አምስቱ አለቆች ባዩት ጊዜ በዚያው ቀን ወደ አስቀሎና ተመለሱ። |
እነዚህም ከግብጽ በስተ ምሥራቅ ካለው ከሺሆን ወንዝ ጀምሮ ወደ ሰሜን እስከ ኤክሮን ድንበር ድረስ ያለው ነው። ይህም በአጠቃላይ ከነዓን ተብሎ ይጠራል። እርሱም የአምስቱ የፍልስጥኤም ማለት የጋዛ፥ የአሽዶድ፥ የአስቀሎና፥ የጋትና የኤክሮን ነገሥታት ግዛት ነው። ሌሎች ያልተያዙ ደግሞ በደቡብ በኩል ያለው የአቢብ ግዛት ነው።
የፍልስጥኤማውያን ገዢዎች ወደ እርስዋ ሄደው እንዲህ አሉአት፤ “ሶምሶንን አግባብተሽ ይህን ሁሉ ብርታት ያገኘው ከምን እንደ ሆነና እንዴትስ አስረን በቊጥጥራችን ሥር በማድረግ ልናሸንፈው እንደምንችል ጠይቂው፤ እያንዳንዳችንም አንድ ሺህ አንድ መቶ ጥሬ ብር እንሰጥሻለን።”
በምድሪቱ ላይ የቀሩትም፥ አምስቱ የፍልስጥኤማውያን መሪዎች፥ ከነዓናውያን በሙሉ፥ ሲዶናውያንና ከባዓልሔርሞን ተራራ አንሥቶ እስከ ሐማት ድረስ በሊባኖስ ተራራዎች የሚኖሩት ሒዋውያን ነበሩ።
ስለዚህም የቃል ኪዳኑ ታቦት ዔቅሮን ተብላ ወደምትጠራው ወደ ሌላይቱ የፍልስጥኤማውያን ከተማ እንዲወሰድ አደረጉ፤ ነገር ግን እዚያ በደረሰ ጊዜ ኗሪዎቹ እየጮኹ በማልቀስ “የእስራኤልን አምላክ የቃል ኪዳን ታቦት ወደዚህ ያመጡብን እኛን ሁላችንን ለመፍጀት አስበው ነው!” አሉ።
ላሞቹም መንገዱን ሳይለቁና ወደ ግራም ወደ ቀኝም ሳያዘነብሉ በቀጥታ ወደ ቤትሼሜሽ በማምራት ጒዞአቸውን ቀጠሉ፤ በሚሄዱበትም ጊዜ እምቧ ይሉ ነበር፤ አምስቱ የፍልስጤማውያን ገዢዎችም እስከ ቤትሼሜሽ ድንበር ድረስ በመከተል ሸኙአቸው።
ሕዝቡም፥ “ስለ በደል የሚከፈል ይሆን ዘንድ ከምን ዐይነት ስጦታ ጋር እንላከው?” ሲሉ ጠየቁ። እነርሱም እንዲህ ሲሉ መለሱላቸው፦ “በእባጩ አምሳል የተሠራ አምስት የወርቅ ጒልቻ፥ እንደ ፍልስጥኤማውያን ገዢዎች ብዛት በአይጥ አምሳል የተሠራ አምስት የወርቅ ጉልቻ መሆን አለበት፤ በእናንተ ሁሉና በአምስቱ ገዢዎች ላይ የተላከው መቅሠፍት አንድ ዐይነት ነው።