ያዕቆብም እንዲህ አለ፤ “ልጆቹ ደካሞች እንደ ሆኑ ጌታዬ ታውቃለህ፤ ለሚያጠቡት እንስሶች፥ ለግልገሎቻቸውና ለእንቦሶቻቸው መጠንቀቅ ይኖርብኛል፤ ለአንድ ቀን እንኳ በጥድፊያ ቢነዱ እንስሶቹ በሙሉ ያልቃሉ።
1 ሳሙኤል 6:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም እንደ ተነገራቸው አደረጉ፤ ሁለት ላሞች ወስደው ሠረገላ በታሰረበት ቀንበር ጠመዱአቸው፤ እንቦሶቻቸውንም ወደ በረት መልሰው ዘጉባቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም እንደዚሁ አደረጉ። ሁለቱን ላሞች ወስደው በሠረገላው ጠመዷቸው፤ እንቦሶቻቸውንም በቤት ውስጥ ዘጉባቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም እንደዚሁ አደረጉ። ሁለቱን ላሞች ወስደው በሠረገላው ጠመዷቸው፤ እንቦሶቻቸውንም በቤት ውስጥ ዘጉባቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፍልስጥኤማውያንም እንዲሁ አደረጉ፤ የሚያጠቡትን ሁለቱን ላሞች ወሰዱ፤ በሰረገላውም ጠመዱአቸው፤ እንቦሶቻቸውንም በቤት ዘጉባቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰዎቹም እንዲሁ አደረጉ፥ የሚያጠቡትን ሁለቱን ላሞች ወሰዱ፥ በሰረገላም ጠመዱአቸው፥ እንቦሳቻቸውንም በቤት ዘጉባቸው፥ |
ያዕቆብም እንዲህ አለ፤ “ልጆቹ ደካሞች እንደ ሆኑ ጌታዬ ታውቃለህ፤ ለሚያጠቡት እንስሶች፥ ለግልገሎቻቸውና ለእንቦሶቻቸው መጠንቀቅ ይኖርብኛል፤ ለአንድ ቀን እንኳ በጥድፊያ ቢነዱ እንስሶቹ በሙሉ ያልቃሉ።
በሰባተኛውም ጊዜ አገልጋዩ ተመልሶ “ከአንድ ሰው መዳፍ የማትበልጥ ትንሽ ደመና ከባሕር ስትወጣ አየሁ” አለው። ኤልያስም “ወደ ንጉሥ አክዓብ ሂድና ‘ዝናቡ ሳያቋርጥህ በፍጥነት ወደ ሠረገላህ ገብተህ ወደ ቤትህ ተመልሰህ ሂድ’ ብለህ ንገረው” ሲል አዘዘው።
ከዚህም በኋላ አካሄዱን ተመልከቱት፤ አቅጣጫው ወደ ቤትሼሜሽ ከተማ ያመራ እንደ ሆነ ይህን አሠቃቂ መቅሠፍት በእኛ ላይ የላከብን እግዚአብሔር መሆኑን ያመለክታል፤ ወደዚያ አቅጣጫ ባያመራ ግን መቅሠፍቱ የመጣብን በአጋጣሚ እንጂ እግዚአብሔር የላከብን አለመሆኑን እንገነዘባለን።”