1 ሳሙኤል 3:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ ዔሊ ዘንድ ሮጦ በመሄድ “ስለ ጠራኸኝ እነሆ! መጥቻለሁ” አለ። ዔሊ ግን “እኔ አልጠራሁህም፤ ተመልሰህ ሂድና ተኛ” አለው፤ ሳሙኤልም ተመልሶ ተኛ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ ዔሊም ሮጦ በመሄድ፣ “እነሆኝ የጠራኸኝ” አለው። ዔሊ ግን፣ “እኔ አልተጣራሁም፤ ተመልሰህ ተኛ” አለው፤ እርሱም ሄዶ ተኛ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ዔሊም ሮጦ በመሄድ፥ “ስለ ጠራኸኝ እነሆ! መጥቻለሁ” አለው። ዔሊ ግን፥ “እኔ አልተጣራሁም፤ ተመልሰህ ተኛ” አለው፤ እርሱም ሄዶ ተኛ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ዔሊም ሮጠ፥ “እነሆኝ ስለ ጠራኸኝ መጣሁ” አለው። እርሱም፥ “አልጠራሁህም፤ ተመልሰህ ተኛ” አለው። ሄዶም ተኛ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ዔሊም ሮጠ፦ እነሆኝ የጠራኸኝ አለው። እርሱም፦ አልጠራሁህም፥ ተመልሰህ ተኛ አለው። ሄዶም ተኛ። |
እግዚአብሔር እንደገና ሳሙኤልን ጠራው፤ ሳሙኤልም ተነሥቶ ወደ ዔሊ በመሄድ “እነሆ! ስለ ጠራኸኝ መጥቼአለሁ” አለው፤ ዔሊ ግን “ልጄ ሆይ! እኔ አልጠራሁህም፤ ወደ መኝታህ ተመልሰህ ተኛ” አለው።