1 ሳሙኤል 19:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ ቤትም ውስጥ ዘልቀው በገቡ ጊዜ ጣዖቱንና በራስጌው ያለውን ከፍየል ጠጒር የተሠራውን ትራስ ብቻ አገኙ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የተላኩትም ሰዎች በገቡ ጊዜ እነሆ፤ የጣዖት ምስሉ በዐልጋው ላይ ተጋድሞ በራስጌውም የፍየል ጠጕር ተደርጎለት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የተላኩትም ሰዎች በገቡ ጊዜ፥ እነሆ፥ የጣዖት ምስሉ በአልጋው ላይ ተጋድሞ በራስጌውም የፍየል ጠጉር ተደርጎለት ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መልእክተኞቹም በገቡ ጊዜ እነሆ፥ ተራፊሙን በአልጋው ላይ አገኙ፤ በራስጌውም ጕንጕን የፍየል ጠጕር ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መልእክተኞቹም በገቡ ጊዜ እነሆ፥ ተራፊሙን በአልጋው ላይ አገኙ፥ በራስጌው ጕንጕን የፍየል ጠጉር ነበረ። |
ሳኦልም ሜልኮልን “ጠላቴ የሚያመልጥበትን ተንኰል በመሥራት ስለምን እንዲህ አታለልሽኝ?” ሲል ጠየቃት። እርስዋም “እኔ ምን ላድርግ፥ ‘ማምለጥ እንድችል ካልረዳሽኝ እገድልሻለሁ’ አለኝ” ስትል መለሰችለት።