1 ሳሙኤል 18:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያን ቀን ጀምሮ ሳኦል ዳዊትን ከእርሱ ጋር እንዲኖር አደረገ፤ ወደ ቤቱም እንዲሄድ አላሰናበተውም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያች ዕለት አንሥቶ ሳኦል ዳዊትን ዐብሮት እንዲኖር አደረገ፤ ወደ አባቱም ቤት እንዲመለስ አላሰናበተውም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያች ዕለት አንሥቶ ሳኦል ዳዊትን አብሮት እንዲኖር አደረገ፤ ወደ አባቱም ቤት እንዲመለስ አላሰናበተውም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ቀን ሳኦል ወሰደው፤ ወደ አባቱም ቤት ይመልሰው ዘንድ አልፈቀደለትም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ቀን ሳኦል ወሰደው፥ ወደ አባቱም ቤት ይመልሰው ዘንድ አልተወውም። |
ስለዚህ ዮናታን ዳዊትን ጠርቶ ይህን ሁሉ ከነገረው በኋላ ወደ ሳኦል አቀረበው፤ ዳዊትም ከዚያ በፊት ያደርገው እንደ ነበር በንጉሡ ፊት እንደ ቀድሞው ማገልገሉን ቀጠለ።