ከዚህ በኋላ ንጉሥ ዳዊት በእግዚአብሔር ፊት ተቀምጦ እንዲህ ሲል ጸለየ፦ “እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፥ እስከዚህ ድረስ ያደረስከኝ፤ እኔ ማን ነኝ? ቤተሰቤስ ምንድን ነው?
1 ሳሙኤል 18:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊትም “የንጉሥ ዐማች እሆን ዘንድ እኔ ማን ነኝ? ቤተሰቤስ በእስራኤል መካከል እምን ቊጥር ይገባል?” ሲል መለሰለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊት ግን ሳኦልን፣ “የንጉሥ ዐማች እሆን ዘንድ እኔ ማን ነኝ? ቤተ ሰቤም ሆነ የአባቴ ጐሣስ በእስራኤል ዘንድ ምንድን ነው?” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊት ግን ሳኦልን፥ “የንጉሥ ዐማች እሆን ዘንድ እኔ ማን ነኝ? ቤተሰቤም ሆነ የአባቴ ወገን በእስራኤል ዘንድ ምንድነው?” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም ሳኦልን፥ “ለንጉሥ አማች እሆን ዘንድ እኔ ማን ነኝ? ሰውነቴስ ምንድን ናት? የአባቴስ ወገን በእስራኤል ዘንድ ምንድን ነው?” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም ሳኦልን፦ ለንጉሥ አማች እሆን ዘንድ እኔ ማን ነኝ? ሰውነቴስ ምንድር ናት? የአባቴስ ወገን በእስራኤል ዘንድ ምንድር ነው? አለው። |
ከዚህ በኋላ ንጉሥ ዳዊት በእግዚአብሔር ፊት ተቀምጦ እንዲህ ሲል ጸለየ፦ “እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፥ እስከዚህ ድረስ ያደረስከኝ፤ እኔ ማን ነኝ? ቤተሰቤስ ምንድን ነው?
እርስዋም ግንባርዋ መሬት እስኪነካ ድረስ እጅ ነሥታ “እኔ ባዕድ ሆኜ ሳለ ስለ እኔ ታስብ ዘንድ እንዴት በፊትህ ሞገስ ላገኝ ቻልኩ?” አለችው።
ስለዚህ የሳኦል ባለሟሎች ይህን ጉዳይ ለዳዊት በምሥጢር ነገሩት፤ እርሱም፦ “እንደእኔ ላለ ዝቅተኛ ድኻ ሰው የንጉሥ ዐማች መሆን ቀላል ይመስላችኋልን?” አላቸው።
ሳኦልም “እኔ ከእስራኤል ነገዶች መካከል በተለይ ታናሽ የሆነው የብንያም ነገድ ተወላጅ ነኝ፤ በዚሁም ነገድ ውስጥ እንኳ የእኔ ቤተሰብ በጣም አነስተኛ ነው፤ ታዲያ እንዲህ ያለውን ጉዳይ ለእኔ ስለምን ትነግረኛለህ?” ሲል መለሰለት።