1 ሳሙኤል 15:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም እርሱና ሠራዊቱ ወደ ዐማሌቃውያን ከተማ ሄደው በአንድ ደረቅ ጅረት ውስጥ ደፈጣ አደረጉ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳኦልም ወደ አማሌቅ ከተማ ሄዶ በአንዲት ሸለቆ ውስጥ አደፈጠ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳኦልም ወደ አማሌቅ ከተማ ሄዶ በሸለቆ ውስጥ አደፈጠ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳኦልም ወደ አማሌቅ ከተማ ወጣ፤ በሸለቆውም ውስጥ ተደበቀ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳኦልም ወደ አማሌቅ ከተማ ወጣ፥ በሸለቆውም ውስጥ ተደበቀ። |
እንዲህ የሚል ትእዛዝ ሰጣቸው፦ “ከከተማይቱ በስተኋላ አድፍጣችሁ ቈዩ፤ ይሁን እንጂ ከከተማይቱ ብዙ ሳትርቁ አደጋ ለመጣል በሚያስችላችሁ ሁኔታ ተዘጋጅታችሁ ጠብቁ፤
ሳኦልም ሠራዊቱን በአንድነት ጠርቶ ጤሌም በሚባል ስፍራ ቈጠራቸው፤ የወታደሮቹም ብዛት ከእስራኤል ሁለት መቶ ሺህ ከይሁዳ ዐሥር ሺህ ሆነው ተገኙ፤
“እስራኤላውያን ከግብጽ በወጡ ጊዜ ቸርነት ስላደረጋችሁላቸው እናንተን ከአማሌቃውያን ጋር እንዳላጠፋ ከዐማሌቃውያን ተለይታችሁ ሂዱ” ብሎ ሳኦል ለቄናውያን ነገራቸው። እነርሱም ከዐማሌቃውያን ተለይተው ሄዱ።