La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ነገሥት 18:30 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከዚህ በኋላ ኤልያስ ሰዎቹን “ወደ እኔ ቅረቡ” አላቸው፤ ሁሉም በዙሪያው ተሰበሰቡ፤ እርሱም ፈርሶ የነበረውን የእግዚአብሔር መሠዊያ በማደስ ሠራው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያም ኤልያስ ሕዝቡን በሙሉ፣ “ወደ እኔ ቅረቡ” አላቸው፤ ሕዝቡም ሁሉ ወደ እርሱ ቀረቡ፤ እርሱም ፈርሶ የነበረውን የእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከዚህ በኋላ ኤልያስ ሰዎቹን “ወደ እኔ ቅረቡ” አላቸው፤ ሁሉም በዙሪያው ተሰበሰቡ፤ እርሱም ፈርሶ የነበረውን የጌታ መሠዊያ በማደስ ሠራው።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ኤል​ያ​ስም ሕዝ​ቡን ሁሉ፥ “ወደ እኔ ቅረቡ” አላ​ቸው። ሕዝ​ቡም ሁሉ ወደ እርሱ ቀረቡ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ኤልያስም ሕዝቡን ሁሉ “ወደ እኔ ቅረቡ፤” አላቸው። ሕዝቡም ሁሉ ወደ እርሱ ቀረቡ። ፈርሶ የነበረውንም የእግዚአብሔርን መሠዊያ አበጀ።

Ver Capítulo



1 ነገሥት 18:30
4 Referencias Cruzadas  

ኤልያስም “ሁሉን የምትችል አምላኬ ሆይ! እኔ ለአምላክነትህ በመቅናት ዘወትር አንተን ብቻ አገለግላለሁ፤ የእስራኤል ሕዝብ ግን ከአንተ ጋር የገቡትን ቃል ኪዳን አፍርሰዋል፤ መሠዊያዎችህንም ሰባብረዋል፤ ነቢያትህንም ሁሉ ገድለዋል፤ እነሆ እኔ ብቻዬን ቀርቻለሁ፤ እነርሱ ግን እኔንም እንኳ ሊገድሉኝ ይፈልጋሉ!” ሲል መለሰ።


ኤልያስም “ሁሉን የምትችል አምላኬ ሆይ! እኔ ለአምላክነትህ በመቅናት ዘወትር አንተን ብቻ አገለግላለሁ፤ የእስራኤል ሕዝብ ግን ከአንተ ጋር የገቡትን ቃል ኪዳን አፍርሰዋል፤ መሠዊያዎችህንም ሰባብረዋል፤ ነቢያትንም ሁሉ ገድለዋል፤ እነሆ እኔ ብቻዬን ቀርቻለሁ፤ እነርሱ ግን እኔን እንኳ ሊገድሉኝ ይፈልጋሉ” ሲል መለሰ።


የእግዚአብሔርንም መሠዊያ በማደስ በላዩ ላይ የኅብረት መሥዋዕትና የምስጋና መባን አቀረበ፤ የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን ያመልኩም ዘንድ መላውን የይሁዳ ሕዝብ አዘዘ።


በዚያን ጊዜ ኤልያስ “ጌታ ሆይ! ነቢያትህን ገደሉ፤ መሠዊያዎችህን አፈረሱ፤ እኔ ብቻ ቀረሁ፤ እኔንም ሊገድሉኝ ይፈልጋሉ” ብሎ ነበር።