1 ቆሮንቶስ 14:30 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በስብሰባ ላይ ለሚገኝ ሌላ ሰው አንዳች ራእይ ቢገለጥለት፤ የመጀመሪያው ተናጋሪ ዝም ይበል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከተቀመጡትም መካከል አንድ ሰው አንድ ነገር ቢገለጥለት፣ የመጀመሪያው ተናጋሪ ዝም ይበል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከተቀመጡትም መካከል አንድ ሰው አንድ ነገር ቢገለጥለት፥ የመጀመሪያው ተናጋሪ ዝም ይበል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ተቀምጦ ሳለ ምሥጢር የተገለጠለት ቢኖር ፊተኛው ዝም ይበል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያ ለሚቀመጥ ለሌላ ግን አንድ ነገር ቢገለጥለት ፊተኛው ዝም ይበል። |
ወንድሞች ሆይ! እንግዲህ ምን ማድረግ ይገባል? ለጸሎት በምትሰበሰቡበት ጊዜ ከእናንተ አንዱ የመዘመር ስጦታ አለው፤ ሌላው የማስተማር ስጦታ አለው፤ አንዱ ስውር የሆነውን ነገር የመግለጥ ስጦታ አለው፤ አንዱ በተለያዩ ቋንቋዎች የመናገር ስጦታ አለው፤ ሌላው የመተርጐም ስጦታ አለው። ታዲያ፥ ይህ ሁሉ ስጦታ ክርስቲያኖችን የሚያንጽ መሆን አለበት።
እንግዲህ ወንድሞች ሆይ! ወደ እናንተ በምመጣበት ጊዜ በተለያዩ ቋንቋዎች እየተናገርኩ ብመጣ ምን እጠቅማችኋለሁ? ይልቅስ የምጠቅማችሁ የእግዚአብሔርን ምሥጢር መግለጥን፥ ዕውቀትን፥ ትንቢት መናገርን፥ ትምህርትን ይዤላችሁ ብመጣ ነው።