የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! እግዚአብሔር በእናንተ ላይ አደጋ የሚጥል ሕዝብ ከሩቅ ያመጣባችኋል፤ ይህም ሕዝብ ቋንቋውን የማታውቁት፥ ንግግሩንም የማታስተውሉት፥ ጥንታዊነት ያለው ብርቱ ሕዝብ ነው።
1 ቆሮንቶስ 14:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም፦ “ ‘በተለያዩ ቋንቋዎች በሚናገሩ ሰዎችና በባዕድ ሰዎች አፍ ለዚህ ሕዝብ እናገራለሁ፤ ይህም ሆኖ አይሰሙኝም’ ይላል ጌታ እግዚአብሔር” ተብሎ በሕግ ተጽፎአል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሕግም እንዲህ ተብሎ ተጽፏል፤ “ቋንቋቸው እንግዳ በሆነ ሰዎች፣ በባዕዳንም አንደበት፣ ለዚህ ሕዝብ እናገራለሁ፤ ይህም ሆኖ አይሰሙኝም፤” ይላል ጌታ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ቋንቋቸው እንግዳ በሆነ ሰዎች፥ በባዕዳንም አንደበት ለዚህ ሕዝብ እናገራለሁ፤ ይህም ሆኖ አይሰሙኝም፥ ይላል ጌታ” ተብሎ በኦሪትም ተጽፎአል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በኦሪትም፥ “ይህን ሕዝብ በሌሎች ቋንቋዎችና በሌላ አንደበት እናገራቸዋለሁ፤ እንዲሁም ሆኖ አይሰሙኝም ይላል እግዚአብሔር” ብሎአል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሌሎችን ልሳኖች በሚናገሩ ሰዎችና በሌላ አንደበት ለዚህ ሕዝብ እነግራቸዋለሁ፥ እንዲህም ቢሆን አይሰሙኝም ይላል ጌታ ተብሎ በሕግ ተጽፎአል። |
የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! እግዚአብሔር በእናንተ ላይ አደጋ የሚጥል ሕዝብ ከሩቅ ያመጣባችኋል፤ ይህም ሕዝብ ቋንቋውን የማታውቁት፥ ንግግሩንም የማታስተውሉት፥ ጥንታዊነት ያለው ብርቱ ሕዝብ ነው።
የሕግ ትእዛዝ የሚመለከተው ከሕግ በታች ያሉትን እንደ ሆነ እናውቃለን፤ በዚህ ምክንያት ሰዎች የሚያመካኙት አጥተው ዝም ይላሉ፤ ዓለሙም ሁሉ በእግዚአብሔር ፍርድ ሥር ይሆናል።