1 ዜና መዋዕል 7:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይሳኮር አራት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ እነርሱም ቶላዕ፥ ፉዋ፥ ያሹብና ሺምሮን ተብለው የሚጠሩት ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የይሳኮር ወንዶች ልጆች፤ ቶላ፣ ፉዋ፣ ያሱብ፣ ሺምሮን፤ በአጠቃላይ አራት ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የይሳኮርም ልጆች፥ ቶላ፥ ፉዋ፥ ያሱብ ሺምሮን፥ አራት ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የይሳኮርም ልጆች፤ ቶላ፥ ፋዋ፥ ያሱብ፥ ሰምሮን፥ አራት ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የይሳኮርም ልጆች ቶላ፥ ፉዋ፥ ያሱብ፥ ሺምሮን፥ አራት ናቸው። |
ቶላዕ ስድስት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ እነርሱም ዑዚ፥ ረፋያ፥ ይሪኤል፥ ያሕማይ፥ ዩብሳምና ሸሙኤል ተብለው የሚጠሩት ናቸው፤ እነርሱም የቶላዕ ጐሣ ቤተሰቦች አለቆችና ዝነኛ ወታደሮች ነበሩ፤ በንጉሥ ዳዊት ዘመነ መንግሥት የእነርሱ ዘሮች ብዛት ኻያ ሁለት ሺህ ስድስት መቶ ነበር።