ረጅም ዕድሜ ቢያገኙ እንኳ ከንቱዎች ይሆናሉ፤ የሽምግልና ዘመናቸውም ያለ ክብር ያልፋል።
ኑሮአቸውም በምድር ላይ ቢበዛ ምንም አይቈጠርም፤ ሽምግልናቸውም በፍጻሜያቸው የጐሰቈለ ይሆናል።