ጦብያም ለአባቱ ለመንገር ወደ ቤት ገባና “እነሆ ከወንደሞቻችን ከእስራኤላውያን አንድ ሰው አግኝቻለሁ” አለው። ጦቢትም “ከየትኛው ቤተሰብና ነገድ መሆኑን ለማወቅና የመንገድ ጓደኛህ ለመሆን እምነት የሚጣልበት መሆኑን ለመገንዘብ እስቲ ሰውዬውን ጥራልኝ ልጄ ሆይ” አለው። ጦብያም ሊጠራው ወጣና “ወንድሜ አባቴ ሊያይህ ይፈልጋል” አለው።
ጠራውና ገባ፤ እርስ በርሳቸውም እጅ ተነሣሡ።