ማሕልየ መሓልይ 8:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ውዴ ሆይ፥ ፍጠን፥ በቅመም ተራራ ላይ ሚዳቋን ወይም የዋላን እምቦሳ ምሰል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ውዴ ሆይ፤ ቶሎ ናልኝ፤ ሚዳቋን፣ ወይም በቅመም ተራራ ላይ የሚዘልል፣ የዋሊያን ግልገል ምሰል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ውዴ ሆይ! ፈጥነህ ወደ እኔ ና፤ የቅመም ተክሎች በሚበቅሉባቸው ተራራዎች ላይ የሚዘል አጋዘን ወይም የዋልያ ግልገል ምሰል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልጅ ወንድሜ ሆይ፥ ፍጠን፤ በቅመም ተራራ ላይ ሚዳቋን ወይም የዋሊያን እንቦሳ ምሰል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ውዴ ሆይ፥ ፍጠን፥ በቅመም ተራራ ላይ ሚዳቋን ወይም የዋላን እምቦሳ ምሰል። |
እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፥ እርሱ እስኪፈልግ ድረስ፥ ፍቅርን እንዳታስነሱትና እንዳታነሣሡት በሚዳቋ በምድረ በዳም ዋላ አስምላችኋለሁ።
“ሆኖም ጌታ አምላክህ በሚሰጥህ መጠን፥ በየትኛውም ከተማህ፥ እንስሳትህን ሚዳቋም ሆነ ድኩላ ዐርደህ የምትፈልገውን ያህል ሥጋ ብላ። በሥርዓቱ መሠረት ንጹሕ የሆነም ሆነ ያልሆነ ሰው ከዚሁ ሥጋ ሊበላ ይችላል።