ወዳጄ ሆይ፥ እነሆ፥ ውብ ነሽ፥ እነሆ፥ አንቺ ወብ ነሽ፥ ዐይኖችሽ በመሸፈኛሽ ውስጥ ርግቦች ናቸው፥ ጠጉርሽ በገለዓድ ተራራ እንደሚወርድ እንደ ፍየል መንጋ ነው።
ማሕልየ መሓልይ 6:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዓይነ ርግብ መሸፈኛሽ ውስጥ ጉንጭና ጉንጭሽ እንደ ተከፈለ ሮማን ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከመሸፈኛሽ ውስጥ ያሉት ጕንጮችሽ፣ ለሁለት የተከፈለ ሮማን ይመስላሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሁለቱ ጒንጮችሽ በፊትሽ ዐይነ ርግብ ውስጥ ሲታዩ ለሁለት የተከፈሉ የሮማን ፍሬ ፍንካች ይመስላሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዝምታሽ በቀር ጕንጮችሽ እንደ ተከፈለ ሮማን ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዓይነ ርግብ መሸፈኛሽ ውስጥ ጕንጭና ጕንጭሽ እንደ ተከፈለ ሮማን ናቸው። |
ወዳጄ ሆይ፥ እነሆ፥ ውብ ነሽ፥ እነሆ፥ አንቺ ወብ ነሽ፥ ዐይኖችሽ በመሸፈኛሽ ውስጥ ርግቦች ናቸው፥ ጠጉርሽ በገለዓድ ተራራ እንደሚወርድ እንደ ፍየል መንጋ ነው።