ማሕልየ መሓልይ 6:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጥርሶችሽ ታጥበው እንደ ወጡ ሁሉ መንታ እንደ ወለዱ ከእነርሱም መካን እንደሌለባቸው መንጎች ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጥርሶችሽ ከመታጠቢያ እንደ ወጡ የበግ መንጋ ናቸው፤ ሁሉም መንታ መንታ የወለዱ፣ ከመካከላቸውም መካን የሌለባቸው ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጥርሶችሽ በመካከላቸው ምንም መኻን ሳይኖርባቸው መንታ መንታ እንደሚወልዱና በውሃ እንደ ታጠቡ ነጫጭ የበጎች መንጋ ደስ ያሰኛሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጥርሶችሽ ታጥበው እንደ ወጡ ሁሉም መንታ እንደ ወለዱ ከእነርሱም መካን እንደሌለባቸው መንጎች ናቸው። ከንፈሮችሽ እንደ ቀይ ሐር ናቸው፥ ቃልሽ ያማረ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጥርሶችሽ ታጥበው እንደ ወጡ ሁሉ መንታ እንደ ወለዱ ከእነርሱም መካን እንደሌለባቸው መንጎች ናቸው። |
በመንገድ ዳር የበለስ ዛፍ አይቶ ወደ እርሷ መጣ፤ ነገር ግን ከቅጠል በስተቀር ምንም አላገኘባትም፤ “እንግዲህ ወዲህ ለዘለዓለም ፍሬ አይገኝብሽ” አላት። የበለስዋ ዛፍም ወዲያውኑ ደረቀች።