ማሕልየ መሓልይ 6:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳላውቅ ነፍሴ በከበረው ሠረገላ ላይ አስቀመጠችኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህን ከማወቄ በፊት፣ ምኞቴ በሕዝቤ ንጉሣዊ ሠረገሎች መካከል አስቀመጠኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳላስበው፥ ምኞቴ በሠረገላ ላይ እንደ ልዑል አስቀመጠኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያ ጡቶችን እሰጥሃለሁ፥ ሰውነቴም አላወቀችም፥ እንደ አሚናዳብ ሰረገላ አደረገኝ አለች። ብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “አይ ዘንድ ... ወረድሁ” ይላል። ወይኑ አብቦ ሮማኑም አፍርቶ እንደ ሆነ ይመለከት ዘንድ ወደ ገውዝ ገነት ወረደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳላውቅ ነፍሴ በከበረው ሰረገላ ላይ አስቀመጠችኝ። |