በዚያም፥ ጌታ እግዚአብሔር ለማየት ደስ የሚያሰኘውን፥ ለመብላትም መልካም የሆነውን ዛፍ ሁሉ ከምድር አበቀለ፥ በገነትም መካከል የሕይወትን ዛፍ፥ መልካምንና ክፉን የሚያስታውቀውንም ዛፍ አበቀለ።
ማሕልየ መሓልይ 6:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የወንዙን ዳር ልምላሜ አይ ዘንድ፥ ወይኑ አብቦ ሮማኑም አፍርቶ እንደሆነ እመለከት ዘንድ ወደ ለውዝ ገነት ወረድሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሸለቆው ውስጥ አዲስ የበቀሉትን አትክልቶች ለማየት፣ ወይኑ ማቈጥቈጡን፣ ሮማኑ ማበቡን ለመመልከት፣ ወደ ለውዙ ተክል ቦታ ወረድሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሸለቆ የተተከሉትን ተክሎች ልምላሜ አይ ዘንድ ወይኑ አቈጥቊጦ፥ ሮማኑም አብቦ እንደ ሆነ ልመለከት ወደ ለውዝ ተክል ቦታ ወረድኩ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልጅ ወንድሜየወንዙን ዳር ልምላሜ ያይ ዘንድ ወይኑ አብቦ ሮማኑም አፍርቶ እንደ ሆነ ይመለከት ዘንድ ወደ ገውዝ ገነት ወረደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የወንዙን ዳር ልምላሜ አይ ዘንድ፥ ወይኑ አብቦ ሮማኑም አፍርቶ እንደ ሆነ እመለከት ዘንድ ወደ ገውዝ ገነት ወረድሁ። |
በዚያም፥ ጌታ እግዚአብሔር ለማየት ደስ የሚያሰኘውን፥ ለመብላትም መልካም የሆነውን ዛፍ ሁሉ ከምድር አበቀለ፥ በገነትም መካከል የሕይወትን ዛፍ፥ መልካምንና ክፉን የሚያስታውቀውንም ዛፍ አበቀለ።
እኅቴ ሙሽራዬ ሆይ፥ ወደ ገነቴ ገባሁ፥ ከርቤዬን ከቅመሜ ጋር ለቀምሁ፥ እንጀራዬን ከማሬ ጋር በላሁ፥ የወይን ጠጄን ከወተቴ ጋር ጠጣሁ። ባልንጀሮቼ ሆይ፥ ብሉ፥ ጠጡ፥ ወዳጆቼ ሆይ፥ እስክትረኩ ድረስ ጠጡ።
እርሱም ቅጠል ያላት የበለስ ዛፍ ከሩቅ አየ፤ ምናልባት ፍሬ ይገኝባት እንደሆነ ብሎ ወደ እርሷ መጣ፤ ነገር ግን የበለስ ወራት አልነበረምና ከቅጠል በቀር ምንም አላገኘባትም።
የወይን አትክልት ሠራተኛውንም ‘እነሆ፥ ከዚህች በለስ ፍሬ ፈልጌ ለሦስት ዓመት ብመላለስ ምንም አላገኘሁም፤ ቁረጣት፤ ስለምን ደግሞ መሬቱን ታጐሳቁላለች?’ አለው።
እኔ መረጥኋችሁ እንጂ እናንተ አልመረጣችሁኝም፤ አብም በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ እንደሚሰጣችሁ፥ እንድትሄዱና ፍሬ እንድታፈሩ ፍሬአችሁም እንዲኖር ሾምኋችሁ።
ከጥቂት ቀንም በኋላ ጳውሎስ በርናባስን “ተመልሰን የጌታን ቃል በተናገርንበት በየከተማው ሁሉ ወንድሞችን እንጐብኛቸው፤ እንዴት እንዳሉም እንወቅ፤” አለው።