መሳፍንቱም ሁሉ እያንዳንዳቸው ሲጠሩ፥ ልባቸው ያልሸፈተ፥ በጌታም ላይ ጀርባቸውን ያላዞሩ፥ መታሰቢያቸው የተባረከ ይሁን።
በየስማቸው የተጠሩ የእስራኤል መሳፍንት፥ ልቡናቸውም ያልሰሰነ ሰዎች ሁሉ፥ እግዚአብሔርንም ያልተዉት ሰዎች ሁሉ፥ ስም አጠራራቸው የተባረከ ይሁን።